የቀረበው የሰላም እቅድ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፍላጎት የተቀረጸ ነው ብለዋል፡፡ የሱዳን ጦር ዩናይትድአረብ ኤምሬትስን ፈጥኖ ደራሽ ሃይሉን በመደገፍ ይከሳታል፡፡
ነገር ግን ይህ ክስ በአረብ ኤምሬትስም ሆነ በፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ በኩል ሀሰት እንደሆነ ነው ተደጋግሞ የሚገለጸው፡፡ የሁለቱ ጀነራሎች ጦርነት ሱዳንን ወደ ከፋ ደረጃ እንዳሸጋገራት ሲነገር፤ከ100ሺ በላይ ሰዎች እንዲገደሉ፤ከ12ሚሊዮን በላይ የሚሆኑትን ደግሞ እንዲፈናቀሉ አድርጓል፡፡
ጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ከአሸማጋዮቹ ውስጥ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እስካለችበት ድረስ ገለልተኛ አይሆንም ብለዋል፡፡
ዩናይትድስቴትስ፡ሳወዲአረቢያ፡ግብጽ፡የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የቀረበውን የሰላም እቅድ ፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ እንደሚቀበለው ሲገልጽ፤የሱዳን ጦር ግን እንደማይቀበለው አስታውቋል፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን ሀገራት ያካተተው ኳድ የተሰኘው የአሸማጋዮች ቡድን ገለልተኛ እንዳልሆነ በሱዳን ጦር በኩል ቅሬታ ይነሳበታል፡፡ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በተደጋጋሚ ፈጥኖ ደራሽ ሃይሉን ትደግፋለች በሚል ክስ ይቀርብባታል፡፡
በዚህ ምክንያት የሱዳን ጦር በኳድ በኩል የቀረበውን የሰላም እቅድ እንደማይቀበለው ገልጻል፡፡ አሁን የዩናይትድስቴትሱ እና የሳውዲ አረቢያው የሰላም እቅድ ዝርዝር ጉዳይ እየተጠበቀ እንደሆነ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡//

