የሲዳማ ክልል ከክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አገኘ

ዛሬ ይፋዊ የክልል መንግስት ምስረታውን በሐዋሳ ከተማ ያካሄደው የሲዳማ ክልል፤ ከተለያዩ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ከ206.5 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ እንዳገኘ ኢፕድ ዘግቧል።
በዚሁ ሥነ-ስርአት ላይ የኦሮሚያ ክልል የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፤ የአማራ ክልል ደግሞ የ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።
በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።የሶማሌ ክልል 10 ሚሊዮን፣ የሀረሪ ክልል 5 ሚሊዮን፣ የአፋር ክልል 7 ሚሊዮን እንዲሁም የጋምቤላ ክልል የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።
በተመሳሳይ የአርሲ ዞን 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፤ የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe