የሳንፍራንሲስኮ ፖሊስ ገዳይ ሮቦቶችን እንዲጠቀም ተፈቀደለት!

የሳን ፍራንሲስኮ ገዥ የሱፐርቫይዘሮች ቦርድ የከተማዋ ፖሊስ ህይወትን ሊያጠፉ የሚችሉ ሮቦቶችን እንዲጠቀም ድምጽ ሰጥቷል።እርምጃው ፖሊስ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ፈንጂ የታጠቁ ሮቦቶችን እንዲያሰማራ የሚያስችል ነዉ፡፡

የፖሊስ ቃል አቀባይ “ሮቦቶች ኃይለኛ፣ የታጠቁ ወይም አደገኛ አካላትን የያዙ ምሽጎችን ለመጣስ ፈንጂ ሊታጠቁ ይችላሉ” ብለዋል።በተጨማሪም ሮቦቶች “የህይወት መጥፋት አደጋ ላይ የሚጥሉ ዓመፀኛ፣ የታጠቁ አደገኛ ተጠርጣሪዎችን ለማዳከም ወይም ለማደናቀፍ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ” ሲሉ አክለዋል።

የህጉን መጽደቅ የሚተቹ ግን የፖሊስ ኃይልን ወደ ጦርነቱ ሊያመራ ይችላል ሲሉ ይነቅፋሉ፡፡ ፖሊስ መኮንኖች ገዳይ ኃይል ያላቸውን ሮቦቶችን መጠቀም የሚችሉት ያላቸዉን አማራጭ የደህንነት ችግር የማስወገድ ስልቶችን ከተጠቀሙ በኋላ ብቻ ነው።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe