የስፖርት ውርርድ ድርጅቶች በ11 ወራት ከ2 በሊየን ብር በላይ ግብር መሰብሰቡ አነጋጋሪ ሆኗል

የስፖርት ውርርድ ድርጅቶች ትኩረታቸውን ወደ ደቡብ የኢትዮጽያ አካባቢዎች ማድረጋቸው ተሰማ፡፡ በደቡብ ኢትዮጽያ አካባቢዎች ብቻ በ11 ወራት ከ2 በሊየን ብር በላይ ግብር መሰብሰቡ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

በአዲስ አበባና በተለያዩ አካባቢዎች ቢሯቸው የተዘጋባቸው የስፖርት ውርርድ አቋማሪ ድርጅቶች ፊታቸውን ወደ ደቡብ የኢትዮጽያ አካባቢዎች ማድረጋቸውን የኢትዮጽያ ሎተሪ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በውርርድ አጫዋቾች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥርን በተመለከተ በቀረበለት የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ ውይይት አድርጓል፡፡

በወቅቱ የኢትዮጽያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ቤዛ ግርማ በአዲስ አበባ፡በድሬዳዋ፡በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በትግራይና አማራ ክልሎች አቋማሪ ድርጅቶች ቢሮ መዘጋቱን ገልጸዋል፡፡

አቋማሪ ድርጅቶች አሁን በደቡብ የኢትዮጽያ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኝ እና በኦንላይንም በስፋት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ባለፉት 11 ወራትም ከአወራራጆቹ የተገኘው የኮሚሽን ገቢ 2.2 ቢሊዮን ብር መድረሱንም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe