የቀድሞው የሊባኖስ መሪ ከእስራኤል ጋር ለመነጋገር ትክክለኛው ስዓት አሁን ነው አሉ

የቀድሞው ፕሬዝዳንት አሚን ገማል እስራኤል እና ሊባኖስ ከ1980 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀጥታ ንግግር ካደረጉ በኋላ ከአሶሼትድ ፕሬስ ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው ይህንን ያሉት፡፡

የቀድሞው ፕሬዝዳንት በእኔ የስልጣን ዘመን ከእስራኤል ጋር ስለ ሰላም ስምምነት መነጋገር ይቅርታ የማያሰጠው ወንጀል ነበረ ብለዋል፡፡

አሁን ግን በቀጠናው አዲስ እይታ የተፈጠረ መስሏል፤ሶሪያ ከእስራኤል ጋር የቀጥታ ንግግር ማድረግ ችላለች፡ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የአብርሃም አኮርድ ስምምነት ለአረብ ሀገራት መቅረብ ጀምሯል፤ዩናይትድአረብ ኤምሬትስም ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመረችበት ዘመን ነው ብለዋል፡፡

አሚን ገማል የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ትጥቁን እንዲፈታ የሚደረገውን ጥረትም እንደሚደግፉ አንስተው፤ባለፉት ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥም ከእስራኤል በደረሰበት ጥቃት አቅሙ ክፉኛ ተዳክሟል ብለዋል፡፡

አሚን ገማል በ1982 መንበረ ስልጣኑን ሲረከቡ ሊባኖስ ለ15 ዓመታት ያህል በዘለቀውና አውዳሚ በነበረው የእርስ በርስ ጦርነት መካከል ውስጥ ነበረች፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሶሪያ እና በእስራል ወታደሮችም የተወረረችበት ዘመን የነበረ ሲሆን የሀገሪቱ ወጣቱ መሪ የነበሩ ሲሆን በወቅቱ እድሚያቸው 40 ዓመት ነበር፡፡

ከዚህ ባለፈም አሜሪካ ሊባኖስን እና እስራኤልን እንድታሸማግል የቀረበውን ሃሳብም የተቀበሉት እሳቸው ነበሩ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን በቅርቡ ከጠቅላይ መሪው ሞጅታባ ካሚኒ ጋር መገናኘታቸውን ገለጹ፡፡

ይህም ከፍተኛው መሪ በዩናይትድስቴትስ እና እስራኤል የጋራ ጥቃት ሳቢያ በደረሰባቸው ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት ከእይታ ርቀው ከቆዩ በኋላ በህይወት ስለሞራቸው የተሰጠ የመጀመሪያው ይፋዊ መግለጫ መሆኑን ታይምስ ኦፍ እስራኤል ጽፏል፡፡

ሞጅታባ ካሚኒ በእስራኤል እና አሜሪካ ጥቃት በየካቲት መጀመሪያ የተገደሉትን አያቶላህ አሊ ካሚንን ተክተው መሾማቸው ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ከሹመታቸው አንስቶ እስካሁን በአካልም ሆነ በቪዲዮ በይፋ ለህዝብ አልታዩም፡፡ እንዲያውም በወቅቱ ሲወጡ የነበሩ አንዳንድ መረጃዎች ሞጅታባ በህይወት ጭምር አለመኖራቸውን የሚገልጹ ነበር፡፡//

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe