የህልፈታቸውን ዜና ያረጋገጠው ካርተር ራሳቸው ያቋቋሙት በዓለም ዙሪያ ዴሞክራሲን እና ሰብዓዊነትን የተመለከቱ ስራዎችን የሚያበረታታው ማዕከላቸው ነው፡፡
“አባቴ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም በሰላም ፡በሰብዓዊነት እና ለሰዎች መኖርን ለሚያምኑ ሁሉ ጀግና ነበር” ያሉት ደግሞ ልጃቸው ቺፕ ካርተር ናቸው፡፡
ጂሚ ካርተር በአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች ታሪክ ረዥም ዓመታት በህይወት የቆዩ እንደሆኑም ይነገርላቸዋል፡፡
100ኛ ዓመታቸውን ጥቅምት ላይ ማክበራቸውም የሚዘነጋ አይደለም፡፡
እሁድ በጆርጂያ መሞታቸው የተሰማው ካርተር የ1979ኙን የካም ዴቪድ ስምምነት በእስራኤል እና በግብጽ መካከል እንዲፈጸም በማድረግ ቁልፍ ሚና በመጫወት ይታወቃሉ፡፡
ዴሞክራቱ ጂሚ ካርተር ከ1977 እስከ 1981 ድረስ በፕሬዚዳንትነት አሜሪካን መርተዋል፡፡
በዕርግጥ ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች በስፋት ይስተዋል እንደነበር ታሪካቸው ልብ ይለዋል።
ካርተር ከነጩ ቤተ መንግስት ከወጡ በኋላ ግን በሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ መስራታቸው የኖቤል የሰላም ተሽላሚ ለመሆን በቅተዋል፡፡

