“የቅርብ ቤተሰቤ አስገድዶ ደፍሮኛል” ስትል በሀሰት የወነጀለችው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣች

 በአክስቱ ሞት ምክንያት ቤታቸው የመጣ የቅርብ ቤተሰቧን ‹‹አስገድዶ ደፍሮኛል›› ስትል በሀሰት በመወንጀሏ ክስ የተመሰረተባት የ16 ዓመቷ ታዳጊ በእስራት ተቀጣች፡፡
የኢፌዲሪ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በዛሬው ዕለት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ (ፌስቡክ) ባጋራው ጽሑፍ እንዳስነበበው በፌደራል የመጀመርያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የቀረበችው ተከሳሽ የሌላን ሰው ንጽህና እያወቀች ማንም ሰው በሌለበት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽሞብኛል በማለት የሐሰት ክስ መስርታለች፡፡ በዚህ ምክንያት ተከሳሹ ድርጊቱ ተፈጸመ ከተባለበት ህዳር 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ህዳር 18 2013 ዓ.ም. ድረስ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆበት በእስር ላይ ቆይቷል፡፡
አቃቤ ሕግ በበኩሉ ተከሳሽ ወንጀሉን እንዳልፈጸመ በማረጋገጡ ከሳሿን ንጹህን ሰው በሐሰት በመወንጀል ወንጀል ከሷታል፡፡ በ1996 ዓ.ም. የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 447/ሀ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ የቀረበለትን የክስ መዝገብ የተመለከተው ፍርድቤት ተከሳሿ ወንጀሉን መፈጸሟን በማመኗ፣ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን የሰው አና የሰነድ ማድረጃ መርምሮ ሀምሌ 07/2013 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፎባታል፡፡ በዚህም መሰረት ተከሳሿ በ2 ወር ቀላል እስራት እና በ100 ብር የገንዘብ መቀጮ እንድትቀጣ ወስኗል፡፡ ዘገባው የኢፌዲሪ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe