የቡና ባንክ ጃክሮስ ቅርንጫፍ ደንበኛ የዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል ዕድለኛ ሆኑ

ቡና ባንክ ላለፉት ወራት ሲያካሂድ የቆየውን ሰባተኛ ዙር “የጭነትና ህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ይቆጥቡ ይሸለሙ” መርሐ ግብር በማጠናቀቁ በመርሐ ግብሩ ላይ ተሳታፊ ለሆኑ ደንበኞቹ ያዘጋጃቸውን በርካታ ሽልማቶች ለእድለኞች ለማስረከብ በብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ የአስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች ፣ የባንኩ ከፍተኛ አመራር አካላት እና ታዛቢዎች በተገኙበት ዕጣ የማውጣት ሥነሥርዓት በይፋ ተካሄዷል።

lottery no
የቡና ባንክ ማርኬቲንግ እና የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አባይነህ ሀብቴ እንደተናገሩት ቡና ባንክ ላለፉት 13 ዓመታት ቁጠባን ባህል ያደረገ ህብረተሰብ እንዲፈጠር ባደረገው ጥረት ከ 2 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን በማፍራት ጠንካራ ማህበራዊ መሰረት መገንባት እንደቻለና የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካትም ከ457 በላይ በደረሱ ቅርንጫፎቹ በመላው ኢትዮጵያ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ የግል ባንክ ነው ብለዋል።
ባንኩ ቀደም ሲል በመደበኛ ታክሲ፣ ሜትር ታክሲና ባጃጅ ሹፌሮችና ባለንብረቶች ላይ ብቻ ተወስኖ የነበረውንና በተከታታይ ለስድስት ዙሮች ሲካሄድ የቆየው ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሐ ግብር በማስፋት ወደ ፈሳሽና ደረቅ ጭነት ማመላለሻ እንዲሁም አነስተኛ፣መካከለኛ እና ከፍተኛ የህዝብ ትራንስፖርት ዘርፍን በማካተት ያሳደገው ሲሆን በዚህም በአጠቃላይ የትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለንብረቶች፣ አሽከርካሪዎችና ረዳቶችን ያካተተ የቁጠባ መርሐ ግብር በመዘርጋት የተሳታፊዎች ቁጥር ከፍ ማድረግ ችሏል።
1ኛ ዕጣ የዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል ባለዕድል አሸናፊ የሎተሪ ዕጣ ቁጥር 4160417 ከጃክሮስ ቅርንጫፍ ሄለን በቀለ ናቸው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe