የቡና ዋጋ መናር መነጋገሪያ ሆኗል፤ በአንድ ወር ውስጥም ከፍተኛ ጭማሬ አሳይቷል

በዚህ ወቀት ቡና በኪሎ 900 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ በአንድ ወር ውስጥም በእጥፍ ጨምሯል ተብሏል፡፡ ለዋጋው መጨመር የገብይት ሰንሰሉ ጤናማ አለመሆን እና የቡና ጠጪዎች ቁጥር ከፍ ማለቱ እንደሆነ የኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ደጀኔ ዳዲ ገልጸዋል፡፡

ከጥቂት ወራት በፊት አንድ ኪሎ ቡና ከ600 ብር ጀምሮ ይሸጥ ነበር የተባለ ሲሆን በዚህ ስዓት እስከ 900 ብር እየተሸጠ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ወደ ገበያ የሚቀርበው የቡና መሸጫ እንደ ጥራቱ የሚለያይ ቢሆንም ከዝቅተኛ  እስከ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው ቡና እስከ 200 ብር የዋጋ ጭማሬ አሳይቷል ተብሏል፡፡

በዚህ ወቅት የቡና ገበሬዎች ህብረት የተቆላ ቡናን ለኢትዮጽያ ምርት ገበያ በ800 ብር ነው የሚያቀርቡት፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe