የባላገሩ ምርጥ የድምጻዉያን ውድድር በመጪው እሁድ ፍጻሜውን ያገኛል ተባለ

 ለአሸናፊዎች በኢትዮጵያ የድምጻውያን ውድድር ታሪክ ከፍተኛውን ሽልማት የሚያስገኘው እንቁ ድምጻውያንን በማፍራት የሚታወቀው ባልገሩ ምርጥ በመጪው እና እሁድ የካቲት 17 ፍጻሜውን ያገኛል።
ለአሸናፊዎች እስከ ስምንት ሚሊየን ብር ሽልማት ያዘጋጀውና በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ አሻራቸውን እያሳረፉ የሚገኙ በርካታ አዳዲስ ድምፃውያንን በማፍራት የሚታወቀው ባላገሩ ምርጥ የሁለተኛ ዙር የድምጻውያን የፍጻሜ ውድድሩን የካቲት 17 2016 አ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ለማካሄድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
የድምጻውያን ውድድሩ በኮቪድ 19 እንዲሁም በአገራዊና አለማቀፋዊ ክስተቶች ሳቢያ በተለይም ተወዳዳሪዎች ከተለያዩ አአገራችን ክፍል የተውጣጡ እንደመሆናቸው በታሰበለት ጊዜ ማጠናቀቅ ያልተቻለ ቢሆንም ተወዳዳሪዎቹ አቅማቸውን እንዲያሳድጉና ለውድድሩ ራሳቸውን አንዲያበቁ በቅርበት ሲያግዝና ሲከታተል መቆየቱን የባላገሩ ቴሌቭዥን ስራ አስፈፃሚ አርቲስት አብርሀም ወልዴ የተናገሩ ሲሆን እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የቀጣዩ ዘመን ብቁ ድምጻውያንን ለህዝባችን ለማስተዋወቅ ተዘጋጅተናል ብለዋል።
ራሳችን ያስቀመጥነውን ከፍ ያለ ደረጃ ለማስጠበቅና ደረጃውን የጠበቀ የፍጻሜ ውድድር ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ያነሳው የውድድሩ ዳኛ የሆነው ሶልጣን ኑሪ ሶፊ በውድድሩም የድምጽ ተወዳዳሪዎችን ከማውጣት ብሻገር በስነምግባር የታነጹ ኢትዮጵያዊ ወግና ባህልን የሚያከብሩ ባለሙያዎችን ለማፍራት የተደረገው ጥረትም ውጤት ማስገኘቱን በመግለጫው ላይ ተናግሯል።
ከመላው የአገሪቱ ክፍል ከተውጣጡ ከሁለት ሺህ በላይ ከሚሆኑ ተወዳዳሪዎች ውስጥ የመጨረሻ 7 ድምጻውያን አሸናፊ ለመሆን በመጪው እሁድ ከፍተኛ ፉክክር እንድሚያደርጉ ሲጠበቅ ለአሸንፊዎች ሽልማትም 8 ሚሊዮን ብር ተዘጋጅቷል።
በዚህም መሰረት አንደኛ ለሚወጣ/ለምትወጣ አሸናፊ አንድ ሚልየን ብር የገንዘብ ሽልማት እና ሁለት ሚሊየን ብር የሚያወጣ አልበም እንደሚሰራለት በጥቅሉ የሦስት ሚሊዮን ብር አሸናፊ የሚሆን ሲሆን
ሁለተኛ ለሚወጣ/ለምትወጣ ተወዳዳሪ ደግሞ 500,000 ብር ሽልማት እና አንድ ሚልየን አምስት መቶ ሺህ ብር የሚያወጣ የሙዚቃ አልበም እንደሚሰራለት በአጠቃላይ የሁለት ሚሊዮን ብር አሸናፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል።
ሶስተኛ ለሚወጣ/ለምትወጣ ተወዳዳሪ 250 ሺህ ብር ሽልማት እና ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር የሚያወጡ ዘፈኖች በጥቅሉ የ አንድ ሚሊዮን ብር ሽልማት ያገኛል ነው የተባለው።
በእለቱ ልዩ ተወዳዳሪዎች የተዘጋጁባቸውን የሙዚቃ ስራዎች በማቅረብ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ታውቋል።
የውድድሩን የተመደበውን ሽልማት ሶስት አገር በቅል ድርጅቶች የሸፈኑ ሲሆን አንደኛ ለሚወጣው ተወዳዳሪ ጊፍት ሪልስቴት ፣ሁለተኛ ለሚወጣ ታፍ ኢነርጂስ እንድሁም ሶስተኛ ለሚወጣ ተስፋዬ የኦቾሎኒ ቅቤ ማምረቻ ድርጅት በመሸፍን ለፍጻሜ ውድድሩ ስኬት ከፍተኛውን ሚና ተወጥተዋል።
የፍጻሜ ውድድሩ በባላጉ ቴሌቪዥን፣በባላገሩ የዩቲዩብና ሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎች በኩል በቀጥታ በአገር ውስጥና በመላው አለም ለሚገኙ ተመልካቾች እሁድ የካቲት 17 ከ8 ሰአት ጀምሮ ለእይታ ይበቃል ።
በአይነቱ ለዩ በሆነ መንገድ በእለቱ በፕሮግራሙ ላይ ለመታደም አንድ ሰው የፈለገውን ያህል የገንዘብ መጠን መክፈል የሚችል ሲሆን ከመግቢያው የሚሰበሰበውም ገንዘብ ለመቄዶንያ የአእምሮ ህሙማንና የአረጋውያን መርጃ ተቋም ይውላል ተብሏል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe