የብሮድካስት ባለስልጣን ከፍተኛ ሀላፊ ከሀገር መኮብልላቸው ተሰማ

ለ11 ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የመገናኛ ብዙሃን ፈቃድና ምዝገባ ዳይሮክተሬት  ዳይሬክተር የነበሩት  አቶ ሙሉጌታ ሲሳይ መንገሻ  ካናዳ ቶሮንቶ ጥገኝነት መጠየቃቸው ተሰማ፡፤

በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የመገናኛ ብዙሃን ፈቃድና ምዝገባ ስራ ላይ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ወገኖች ፈቃድ የሚሰጠው እሳቸው የሚመሩት ዳይሮክተሬት እንደሆነ የሚናገሩት ዳይሬክተሩ  በተለይ የመንግስት ባለስልጣት ተፅእኖ ይደረግ እንደነበር ገልጠው በተለይም ለፖለቲካው ቅርበት ላላቸው ወገኖች ከህጉ ውጭ ፈቃድ እንዲሰጣቸው ግፊት ይደረግ እንደነበር በካናዳ ቶሮንቶ እየተዘጋጀ በ143 ሀገራት በኢንተርኔት በሚደመጠው ከራዲዮ መገናኛ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልስ ገልፀዋል፡፡

እንደ ዋልታ ያሉ ለመንግስትና ለገዢው ፖርቲ ቅርበት ያላቸው ሚዲያዎች ህጉ ከሚያዘው ውጭ በፍጥነት ፍቃድ እንዲሰጣቸው ግፊት ከመደረጉም በላይ ዋልታ ፈቃድ ሳይሰጠው የቴሌቪዥን ስርጭት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በህግ ከተሰጠው ሃላፊነት አልፎ በህትመት ስራዎች የይዘት ቁጥጥር ውስጥ ይገባ እንደነበር የጠቀሱት አቶ ሙሉጌታ መንግስትን ይተቻሉ ተብለው በተፈረጁ የህትመት ውጠቶች ላይ የህትመት ትንተና እየሰራ ለመንግስት ያቀርብ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

በብሮድካስት ሚዲያዎች ላይም በይዘት ትንተና ሰበብ የተለያዩ አስተዳዳራዊ ተፅእኖዎች ይደረግ እንደነበር የተናገሩት ባለስልጣኑን በዋና ዳይሬክተርነትና በምክትል ዳይሬክተርነት ደረጃ ለረዥም ዓመታት ከአንድ ብሔርና የፖለቲካ ድርጅት የተመደቡ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ባለፉት 11 ዓመታት ከሚዲያ ፈቃድ ጋር በተያያዘ ህጉን ለማስፈፀም ሲሞከር ሠራተኞችን ላይ ፍረጃዎች ይደረግ እንደነበር የሚናገሩት ሀላፊው መንግስትን የሚቃወሙ ጋዜጠኞች የጋዜጣና መፅሔት ፍቃድ እንዳያገኙ በስውር እጆች ተፅእኖ ይደረግ ነበር ብለዋል፤

ከለውጡ በኋላም የብሮድካስት ባለስልጣን ህጉን ተከትሎ መስራት ባለመቻሉና የፖለቲካ ተፅእኖው እየበረታበት መምጣቱን የሚናገሩት አቶ ሙሉጌታ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩና የሚያጫርሱ ሚዲያዎች እንደፈለጉ እንዲሰሩ እየተደረገ ሚዛናዊ መረጃ በሚያቀርቡት ሚዲዎች ላይ የሚደረገው ጫና ሊቆም ስላልቻለ ሀገር ጥለው ለመሰደድ መገደዳቸውን ተናግረዋል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe