ቦርሳ ከመታወቁ አስቀድሞ እናቶቻችን መቀነትን ለገንዘብ መያዣነት ይጠቀሙበት ነበር፡፡ ቀስ በቀስ ቦርሳ ከገንዘበ መያዣነት ይልቅ በፋሽንነት ይደረግ ጀመር፡፡ የቦርሳ አሰራርም እድገትም ሆነ ጥበብ መታየት ጀመረ፡፡ የቦርሳ ፋሽን በየጊዜው የሚለዋወጥ ሲሆን ከወቅቱ፣ ከቦታውና ከአለባበስ ጋር የሚሄዱ ቦርሳዎች የጊዜው ፋሽን ይባላሉ፡፡
የልጃገረዶች ቦርሳ
ከ10-18 ዓመት ዕድሜ ክልል ላሉ ልጆች የሚሆን ቦርሳ ነው፡፡ ይህ ቦርሳ አነስ ብሎ የተወሰነ ዕቃ ብቻ መያዝ የሚችል ሲሆን ማንገቻው ረጅም ቢሆን ወይም በጀርባ ሊታዘል የሚችል አነስተኛ ቦርሳ ነው፡፡
የግብዣ ቦርሳ
የግብዣ ቦርሳ ለግብዣና ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚደረግ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ጌጥ የበዛባቸው እና ከተለያዩ ጨሌዎች፣ ዶቃዎች ፣ መስታውቶች ፣ ከሐር ጨርቆች እና ከቀላል ብረቶች የሚሰሩ ናቸው፡፡ በተለያዩ ቀለማት የተዋቡ በመሆናቸው ውበታቸው ጎልቶ ይታያል፡፡ እነዚህ ቦርሳዎች በሚደረጉበት ጊዜ ለሚለበሰው ልብስና ጫማ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ከልብስና ከጫማ ቀለም ጋር አብሮ የሚሄድ ቦርሳም መምረጥ ያስፈልጋል፡፡ ከልብስ ወይም ከጫማ ቀለም ጋር ተመሳሳይነት ያለው ቦርሳ ካልተገኘ ጥቁር ቦርሳ መጠቀም ይመረጣል፡፡
ይህም ጥቁር ቦርሳ ከማንኛውም ቀለም ጋር የሚሄድ ስለሆነ ነው፡፡ በፊት በፊት ሙሽሮች በሰርጋቸው ዕለት ነጭ ቦርሳ እንደ ፋሽን ይይዙ ነበር፡፡
የሙሽራ ቦርሳዎች በቆዳ፣ በሐር ፣ በነጭ ጨሌ የሚሰሩ ነበሩ፡፡ መጠኑን አነስ ብሎ ክንድ ላይ ይንጠለጠል ነበር፡፡ ቦርሳ ለሙሽሪት በጣም አስፈላጊ በመሆኑ በጥሎሽ ላይ እንኳ ካልታየ ቅሬታ ይፈጥራል፡፡
የዕረፍት ቀን ቦርሳ
የዕረፍት ቀን ቦርሳ በመባል የሚታወቁት ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየተለመዱ መጥተዋል፡፡ ከሰኞ እስከ አርብ የምንይዘው ቦርሳም ለማሳረፍ ይጠቅማሉ፡፡ አሰራራቸውም ብዙውን ጊዜ ቀለል ያለና ክብደት የሌለው ነው፡፤ በዕረፍት ቀን ከሚለበሱ ጅንስና ቱታ ጋር አብረው
ሲደረቡ ውበታቸው ጎልቶ ይታያል፡፡ ከጅንስ ፣ ከሸራ ፣ ከወፍራም ፕላስቲክና ከሳጠራ የሚሰሩ ሲሆን ብዙ ጊዜ ሰፋ ብለው ረዘም ያሉ ናቸው፡፡ ቀለማቸውም በአብዛኛው ልሙጥ ነው፡፡
ፋሽንና ውበት
እነዚህ ቦርሳዎች ከሽርሽር ቦርሳዎች ጋር ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ዋና የምናዘወትር ከሆነ ቦርሳችን ውስጡ ፕላስቲክ ሊኖረው
ይገባል፡፡ ምክንያቱም እርጥበት ያላቸው ነገሮች ለማስቀመጥ ይረዳናል፡፡ ቦርሳችን በእርጥበት እንዳይበላሽ ያደርጋል የጉዞ ቦርሳ ከሽርሽር ቦርሳ የሚመሳሰል ሲሆን በመጠን ከፍ ያለ ነው፡፡ የተለያዩ ዕቃዎችንም ለመያዝ የተለያዩ ኪሶች ሊኖሩት ይገባል፡፡ በጉዞ በሚቆዩበት ጥቂት ቀናት የሚቋጥሩትን ልብሶች የሚይዝ መሆን አለበት፡፡ ጠንከር ያለ እና ረጅም ማንገቻም ሊኖረው ያስፈልገል፡፡
ቦርሳው በጀርባ የሚታዘል ቢሆን ደግሞ ረጅም ማንገቻ ሊኖረው ያስፈልጋል፡፡ ጠቆር ያሉ ቀለማቸው በቶሎ አቧራ የማይቆሽሹ ተመራጭ ናቸው፡፡
የሜካፕ ቦርሳ
ይህ ቦርሳ የተለያዩ መዋቢያ እቃዎችን ለመያዣነት የሚያገለግል ነው፡፡ ሜካፕ ቦርሳ ውስጥ እንዳይደፋና ቦርሳ እንዳይበላሽ እነዚህ ቦርሳዎች ይረዳሉ፡፡ ይህ ቦርሳ ከሐር ጨርቅና ከስስ ቆዳ ይሰራል፡፡ የሜካፕ ቦርሳ አነስ ያለ ሲሆን ቢቆሽሽ እንኳን በቀላሉ ሊታጠብ የሚችል ነው፡፡ የሜካፕ ቦርሳ የሌላት ሴት ገበሩ በኩል ፣ በሊፒስቲክ ፣ በፓውደር በተለያዩ ሜካፖች መበላሸቱ የማይቀር ነው፡፡ እንዲሁም ራስን ለማስዋብ
የሚወስደውን ጊዜ ይቆጥባል፡፡ ስለዚህ ማንኛዋም ሴት የቦርሳ ደህንት ተጠብቆ እንዲቆይ የሜካፕ ቦርሳን ልትጠቀም ይገባል፡፡
ልክ እንደ አለባበስ ሁሉ የምንይዘው ቦርሳ ተስማሚያችን መሆኑን በቅድሚያ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ አጭር ሴት ረጅም ማንገቻ ያለው ቦርሳ ልትይዝ አይገባትም፡፡ የቦርሳው ርዝመት ከወገቧ ማለፍ አይኖርበትም፡፡ አጭር ማንገቻ ያላቸው ቦርሳዎች ልትመርጥ ይገባል፤ የቦርሳው ስፋትም ሆነ ርዝመት መጠነኛ መሆን አለበት፡፡
የቦርሳ ፋሽን

