የትራምፕ የሰላም ዕቅድ፤ ድጋፍና ተቃውሞ

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለረጅም ጊዜያት ሲጠበቅ የነበረውን የመካከለኛው ምሥራቅ የሰላም ዕቅዳቸውን ይፋ ካደረጉ ሳምንታት ተቆጥረዋል፡፡ ዕቅዱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ይረዳል ተብሎ የተዘጋጀ ነው፡፡ እርሳቸው ‹የክፍለ ዘመኑ ምርጥ ስምምነት› ያሉት የሰላም ዕድቅ ከእሥራኤል ጋር መግባባት ላይ የተደረሰበት ቢኾንም ከፍልስጤማውያን ግን ምንም ዓይነት ሐሳብ በግብዓትነት ሳይካተትበት ነው የጸደቀው፡፡ የፍልስጤም አስተዳደር ዕቅዱ ገና ከመጽደቁ በፊት ለእሥራኤል ያደላ መኾኑን አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይፋ ከኾነ በኋላም የእሥራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ ‹የእሥራኤልን የመጨረሻ ድንበሮች የሚወስን ታሪካዊ ዕቅድ ነው› ሲሉ ማድነቃቸው በእርግጥም እሥራኤልን ተጠቃሚ ለማድረግ የተዘጋጀ መኾኑን ሳይጠቁም አልቀረም፡፡
የፍልስጤም ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች የትራምፕን ዕቅድ እስከመጨረሻው ድረስ እንደሚፋለሙት ተናግረዋል፡፡ በምሥራቅ ኢየሩሳሌም የሚኖሩት ፋክሪ አቡ ዲያብ የተባሉ ፍልስጤማዊ አክቲቪስት ‹ትራምፕ የባልፉርን ስምምነት መልሰው በማምጣት ታሪክን እየደገሙ መኾኑ ግልጽ ነው፡፡ ትራምፕ የራሳቸው ያልኾነን ነገር ለመጠቀም መብት ለሌለው ሕዝብ እየሰጡ ነው› ሲሉ ተቃውመውታል፡፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከእሥራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አጠገብ ተቀምጠው በቤተመንግሥታቸው ዕቅዱን ይፋ ሲያደርጉ ሁለቱንም አካላት ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደኾነ ተናግረው ነበር፡፡ የሰላም ዕቅዱ እሥራኤልና ፍልስጤምን ወደተሻለ መንገድ መምራት የሚችል ነው፡፡
የትራምፕ ዕቅድ ምሥራቅ ኢየሩሳሌምን የፍልስጤም ዋና ከተማ የሚያደርግና ሀገሪቱ ኤምባሲዋን በዚያ እንደምትከፍት የሚገልጽ ነው፡፡ ኢየሩሳሌምን ደግሞ የእሥራኤላውያን ያልተከፋፈለች ከተማ ያደርጋል፡፡ ‹‹የዩናይትድ ስቴትስ ሐሳብ ፍልስጤማውያን በውጪ ሀገራት ዕርዳታ ላይ መደገፋቸው እንዲቆም ነው›› ሲሉም ተናግረዋል ዶናልድ ትራምፕ፡፡ እቅዱ በእስራኤል ተወርሮ ያለውን አብዛኛውን ዌስት ባንክ እንድትቆጣጠር ለእሥራኤል እውቅና የሚሰጥ ነው፡፡
የእሥራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ዕቅዱ ይፋ የኾነበትን ቀን እ.ኤ.አ ግንቦት 14 ቀን 1948 የወቅቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ሐሪ ትሩማን ለእሥራኤል ዕውቅና ከሰጡበት ቀን ጋር አነጻጽረውት ‹ታሪካዊ ቀን› ብለውታል፡፡ ‹‹ትራምፕ በጁዲያ ሳማሪያ፣ በዮርዳኖስ ሸለቆ እና በሌሎች ስትራቴጂያዊ ቦታዎች ላይ የእሥራኤልን ሉዓላዊነት ዕውቅና የሰጡ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ናቸው›› ሲሉም አወድሰዋቸዋል፡፡
‹ፍልስጤም ለሽያጭ አትቀርብም› በሚል ቁጣ በጋዛ ሠርጥ ተቃውሟቸውን የገለፁት በሺህ የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን በበኩላቸው የትራምፕ እና የኔታንያሁን ፎቶግራፎች አቃጥለዋል፡፡ ፕሬዚዳንት መሐሙድ አባስም ፍልስጤም ዕቅዱን ፈጽሞ እንደማትቀበለው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ተገኝተው ተናግረዋል፡፡ ይህን አቋም የእስላማዊ ሀገራት ትብብር ድርጅት የኾነው አረብ ሊግ እና የአፍሪካ ህብረትም እንደሚደግፉት ነው ያስታወቁት፡፡
ሌሎች ሀገራት ምን አሉ?
በሰላም ዕቅዱ ላይ አስተያየታቸውን ከሰጡ የተለያዩ ሀገራት መካከል አንዳንዶቹ ዕቅዱ ለአንድ ወገን ያደላ ነው ሲሉ ኮንነውታል፡፡ ሌሎች ደግሞ ለሁለቱ ሀገራት የረጅም ዓመታት ጦርነት መፍትሔ የሚሰጥ ነው ሲሉ አድናቆት ችረውታል፡፡ ፓኪስታን በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ባወጣችው መግለጫ የፍልስጤማውያን ጉዳይ የሚቋጭበትን መንገድ የምትደግፍ መኾኗን ይፋ አድርጋለች፡፡ ይህ የሚኾነውም የፍልስጤማውያንን በራስ የመወሰን መብት በማክበርና ሕጋዊ መብቶቻቸውን በውይይትና በስምምነት በማረጋገጥ ነው ብላለች፡፡ ፈረንሳይ የትራምፕን የሰላም ዕቅድ በጥንቃቄ እያጠናች መኾኑን ጠቁማለች፡፡ በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን በዓለማቀፍ ሕግጋት ላይ መሠረት ያደረገና በሁለቱም ሀገራት በኩል ተቀባይነት ያለው ስምምነት ያስፈልጋል ብላለች፡፡
የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን ‹‹ዕቅዱ የፍልስጤማውያንን መብት የተጋፋ እና ለእስራኤልን ወረራ ይሁንታ የሰጠ ነው›› ሲሉ ተቃውመውታል፡፡ ‹‹ኢየሩሳሌም የሙስሊሞች ቅዱስ ስፍራ ናት፡፡ ኢየሩሳሌምን ለእሥራኤል መስጠት በፍፁም ተቀባይነት የለውም›› ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናረዋል፡፡ የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር ለእሥራኤል – ፍልስጤም የረጅም ዓመታት ግጭት መፍትሔ ለማምጣት ያደረገውን ጥረት ያደነቀችው ኳታር መፍትሔው ከዓለማቀፍ ሕግጋት ጋር የተጣጣመ መኾን እንዳለበት አስታውሳለች፡፡ የፍልስጤማውያን መብት ካልተከበረ ሰላም መስፈን እንደማይችልም ነው የገለጸችው፡፡
ኢራን በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ባወጣችው መግለጫ ‹‹አሜሪካ በፍልስጤማውያን ላይ የጣለችው አሳፋሪ የሰላም ዕቅድ የክፍለ ዘመኑ ክሕደት ነው›› ብላለች፡፡ ዮርዳኖስም እንዲሁ ባወጣችው መግለጫ ለእስራኤል በመወገን የሚካሔዱ ተግባራት ከፍተኛ ቀውስ እንደሚያስከትሉ ማሳሰብ መርጣለች፡፡ ‹አማን› በተሰኘች የሀገሪቱ ዋና ከተማ የፕሬዚዳንት ትራምፕን የሰላም ዕቅድ ተቃውመው የወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞች ‹‹ለእሥራኤል ዕውቅና አንሰጥም›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ግብፅ እና ሳዑዲ አረቢያ ትራምፕ የሰላም ዕቅዱን ማዘጋጀታቸውን አድንቀው የሀገራቱ የዘመናት ግጭት በውይይትና በስምምነት ብቻ መፈታት እንደሚገባው አመልክተዋል፡፡ እንግሊዝ በበኩሏ ዕቅዱ ተገቢ ነው የሚል አቋም ይዛለች፡፡
ለምን አሁን?
የትራምፕ የሰላም ዕቅድ በዚህ ወቅት የወጣው ለምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ መነሻ አድርጋ የአልጀዚራዋ ጋዜጠኛ መርሲሐ ጋዞ ተከታዮቹን ምላሾች ሰጥታለች፡፡ የመጀመሪያ ምክንያት አድርጋ የጠቀሰችውም የእሥራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የገቡበትን አጣብቂኝ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በድጋሚ ለመመረጥ የምረጡኝ ዘመቻ ውስጥ የሚገኙ ቢኾንም የሙስና ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ነው፡፡ ኔታንያሁ ላይ በጉቦ፣ በማጭበርበርና በእምነት ማጣት ሦስት የተለያዩ ክሶች ቀርበዋል፡፡ ስለዚህ ሁለቱ መሪዎች ይህን ርዕሰ ጉዳይ በመቀየር የእሥራኤላውያን ትኩረት ከኔታንያሁ የሙስና ክስ ወደ ትራምፕ የሰላም ዕቅድ እንዲዞር ይፈልጋሉ፡፡
ለእሥራኤል ወግኗል የተባለለትና በአፍሪካ ሕብረት እና በአረብ ሊግ ተቀባይነት ያጣው የዶናልድ ትራምፕ የሰላም ዕቅድ መጨረሻ ምን ይኾን? መጨረሻውን መጪው ጊዜ ያሳየናል፡፡

መስሪያ ቤቱ የቅርስ ጥበቃ ባለሙያ ጋር ቃለመጠይቅ የሚያደርግ ስለሆነ በእናንተ በኩል አስፈላጊውን ትብብር እና ድጋፍ እንድታደርጉልን እጠይቃለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

ግልባጭ፡-
ለቴሌቪዥን ዘርፍ
ለዶክመንተሪ ዲፓርትመንት
ኢቢሲ፡-

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe