‘የትዳር አጋሬ ገበያ ሄዳ አልተመለሰችም’ ያለው ባል በግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ተያዘ

የትዳር አጋሬ ገበያ ሄዳ አልተመለሰችም ያለው ባል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ነው።
#በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን በገዋታ ወረዳ ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ወረዳው ፖሊስ ዘንድ ቀርቦ የትዳር አጋሬና የልጆቼ እናት ሚያዚያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ ገበያ ለግብይት ሄዳ አልተመለሰችም ጉዳዩን ፖሊስ ይወቅልኝ በሚል ቀርቦ ማስመዝገቡ ነው ፡፡
#እንደ ፖሊስ አዛዥ ዮሐንስ ገለፃ ይኸው ግለሰብ ሚያዚያ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ በድጋሚ ፖሊስ ዘንድ ቀርቦ የጠፋችውን የባለቤቴን አስክሬን ጫካ ውስጥ አገኘው ብሎ ሊያመለክት በመጣበት ፖሊስ በቁጥጥር ስር አድርጎት አስክሬኑን በጥንቃቄ በማንሳት ለህክምና በመላክ መረጃና ማስረጃ ማፈላለጉን አስረድተዋል፡፡
#ባል ሚስቴ ጠፋች ብሎ አስመዝግቦ አስክሬኗን አገኘሁ ማለቱ ወንጀሉን ሳይፈፅም እንዳልቀረ ከውሳኔ ደርሰው ፖሊስ የተጠርጣሪ ደሳለኝ ወርቁ ከገዋታ ወረዳ ፍርድ ቤት የብርበራ ትዕዛዝ በመያዝ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ በተደረገው ብርበራ ለወንጀል የተፈፀመበት የደረቀ ደም ያለበትን አንድ ጦር እና ገጀራ መገኘቱን ጠቁመዋል፡፡መርማሪው ፖሊስ ግለሰቡ በሰጠው የእምነት ቃል እንዳረጋገጠው ሚስት ገበያ ውላ ስትመለስ ባል በወረዳው መዳቦ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጎጀብ ወንዝ ድልድይ አከባቢ ተደብቆ መንገድ በመጠበቅ ሚያዚያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ላይ አስቀድሞ ለወንጀሉ መፈፀሚያ ባዘጋጀው ገጀራ ቀኝ እጅዋ ላይ መቶ ከሰበረ በኋላ እንዳትጮህ በለበሰችው ጥምጣም በማነቅ በያዘዉ ገጀራ ጭቅሏትዋ ላይ ሦስት ቦታ በመቁረጥ በቀኝ እና በግራ ጎንዋ ላይ አንድ ጊዜ በመቁረጥ በቀኝ ጡትዋ ላይ አንድ ጊዜ በመቁረጥ ከባድ ጉዳት በማድረሰ ከገደላት በኋላ የወንጀል ድርጊቱ እንዳይታወቅበት ፖሊስ ዘንድ ቀርቡ ማስመዝገቡን ፖሊስ በምርመራው ማረጋገጡን አስረድተዋል፡፡
#የታክቲክ ምርመራ የስራ ሂደት አስተባባሪ ረዳት ኢንስፔክተር ሙሉጌታ መለሰ የወንጀሉ መንስኤ በተመለከተ ጠይቀናቸው ተጥርጣሪው የግል ተበዳይ እና የሁለት ልጆቹ እናት ጋር ዘወትር በመካከላቸዉ ጭቅጭቅ መኖሩን የጠቆመው ፖሊስ የግል ተበዳይ ሟች ከመጀመሪያው ባለቤቷ ጋር በትዳር ሲኖሩ ሶስት ልጆችን ከወለዱ በኃላ ማግባቱንና ሁለት ልጆችን መወለዳቸውን ገልፆ ከቀድሞ ባለቤቷ ጋር ትማግጣለች በሚል ጥርጣሬ በመነሳት ወንጀሉን መፈፀሙን ለፖሊስ የሰጠው የእምነት ቃሉን በወንጀል ስነስርዓት ቁጥር 35 እንዲያረጋግጥ መደረጉን ገልፀዋል፡፡ፖሊስ በመጨረሻም በተጠርጣርዉ ላይ ያጣራውን የምርመራ መዝገቡ በግለሰቡ የእምነት ቃል፤በህክምና ማስረጃና ለወንጀሉ የተፈፀመበትን ጦርና ገጀራ እግዝቪት በማደራጀት ክስ እንዲመሰረትበት ለዐቃቤ ህግ እንደሚላክ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe