ክልሎች ለብሔራዊ ባንክ የሚያቀርቡት የወርቅ መጠን ጨምሯል ተባለ፡፡ ማዕከላዊ ባንኩ ከ45 ኪ.ግ በላይ ወርቅ ለሚያቀርቡ ክልሎች የሚሰጠው ማበረታቻ ለመጨመሩ ምክንያት ነው እንደሆነ ተገልጻል፡፡ የትግራይ ክልል በ2017 በጀት ዓመት 189 ኩንታል ወርቅ አስገባሁ ማለቱ አነጋጋሪ የሆነ ሲሆነ በዚህም ከ250 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማድረግ እንደቻለም ተሰምቷል፡፡ ብሄራዊ ባንክ ግን ትግራይ አስገባሁ ስላለው የወርቅ መጠን ማረጋገጫ አልሰጠም፤ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 4ሺ700 ኪ.ግ ወርቅ ያስገባ ሲሆን 49 ሚሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል፡፡ በተጨማሪ የአፋር ክልል 225 ኪ.ግ ወርቅ አስገብቶ 350 ሚሊዮን ብር ገቢ ሰብስቧል፡፡//
የትግራይ ክልል በ2017 በጀት ዓመት 189 ኩንታል ወርቅ አስገባሁ ማለቱ አነጋጋሪ ሆነ

