“የትግራይ ክልል አሁንም ድረስ የጭቆና አገዛዝና አፈና ተጠናክሮ ቀጥሏል” ትዴፓ

“የትግራይ ሕዝብ እየደረሰበት በሚገኘው ጭቆና እንደሌላው የአገሪቱ ሕዝብ ተደራጅቶ መብቱን ማስከበር አልቻለም” ሲል የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) ገለጸ።

ፓርቲው የኮሮና ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከመከሰቱ በፊትም ምርጫው እንዲራዘም ሲሞግት መቆየቱን አስታውሶ የተላለፈውን ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ እንደሚቀበለው አስታውቋል።

Read also:ኢትዮጵያ ለኮረና ቫይረስ ፈውስ የሚሆኑ 45 ባህላዊ መድሃኒቶች ላይ ሳይንሳዊ ምርምር…

የፓርቲው ሊቀ-መንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ መግለጫ ሲሰጡ “የትግራይ ክልል አሁንም ድረስ የጭቆና አገዛዝና አፈና ተጠናክሮ ቀጥሏል” ነው ያሉት።

ሕዝቡ ተደራጅቶ መብቱን ለምን አያስጠብቅም የሚሉ ጥያቄዎች ከተለያዩ አካላት ይነሳሉ ያሉት ዶክተር አረጋዊ፤ መብት ለመጠየቅ ሙከራ በሚያደርጉት ላይ የሚደርሰውን እንግልት በማየት ዝምታን መምረጡን ይናገራሉ።

ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ሆነ ሕዝቡ ተደራጅቶ እንቅስቃሴ ማድረግ የማይችሉበት ሁኔታ ላይ መሆናቸውን የገለጹት ዶክተር አረጋዊ፤ ጭቆናውን በመቋቋም ተቃውሞ ሊያሰሙ የሞከሩ ኃይሎች ላይ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።

Read also:ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ደረጃ የውሃ ሙሌት ለመጀመር  የግብፅን ይሁንታ እንደማትፈልግ ለፀጥታው ምክር…

በዚህም እንደ ሌላው አካባቢ ሕዝቡ ተደራጅቶ መብቱን ማስከበር አለመቻሉን ገልጸዋል።

እንደ ሊቀመንበሩ ገለጻ ፓርቲያቸው የኮሮና ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከመከሰቱ በፊት ጀምሮ ምርጫው ይራዘም የሚል አቋም ይዟል።

ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ለምርጫ ወሳኝ ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸው፤ ይህ ባልተሟላበት ሁኔታ ምርጫ መካሄድ እንደሌለበት ሞግተናል ብለዋል።

Read also:በአረንጓዴ አሻራ ከተከተሉት ችግኞች 84 በመቶ የሚሆኑት መጽደቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ…

”ገዥው ፓርቲ ምርጫውን ለማራዘም የወሰነው ውሳኔ የወቅቱን ሁኔታ ያገናዘበ በመሆኑ ያለምንም ጥያቄ እንቀበለዋለን” ብለዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe