የቶክዮ ኦሎምፒክ ለዓለም አቀፍ ደጋፊዎች ዝግ መሆኑ ተገለፀ

የቶክዮ ኦሎምፒክ ከፊታችን ሐምሌ 16 ጀምሮ እንደሚካሄድ ይጠበቃል!

በኦሎምፒኩ ላይ ከ200 ሀገራት የተውጣጡ ከ11 ሺህ በላይ አትሌቶች ይሳተፋሉ

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ዓለም አቀፍ ታዳሚዎች የ2020 የቶክዮ ኦሎምፒክ ጨዋታዎችን መከታተል እንደማይችሉ ተነግሯል።

የጃፓን ባለስልጣናት ለቶክዮ ኦሎምፒክ እና ፓራ ኦሎምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ እንዳስታወቁት ለውድድሩ ወደ ሀገሪቱ በሚገቡት ለይ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል።

የቶኪዮ ኦሎምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴም እርምጃው ደህንነቱ የተጠበቀ ውድድርን ከማድረግ አንጻር ለውድድሩ ተሳታፊዎች እና ለጃፓን ህዝብ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።

በቶክዮ ኦሎምፒክ ላይ ዓለም አቀፍ ደጋፊዎች እንዳይገቡ ክልከላው የተላለፈው ቀደም ብለው በኦሎምፒኩ ላይ ለመሳተፍ ትኬት ቆርጠው በመጠባበቅ ላይ ለነበሩ ግልጽ የሆነ ውሳኔ ለማሳወቅ መሆኑንም አዘጋጆቹ ተናግረዋል።

በኦሎምፒኩ ለይ ለመሳተፍ ቀደም ብለው ትኬት ቆርጠው በመጠባበቅ ላይ ለነበሩ በሙሉ ገንዘባቸው ተመላሽ እንደሚደረግም አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

የ2020 የቶክዮ ኦሎምፒክ ባሳለፍነው ዓመት እንዲካሄድ መርሃ ግብር ወጥቶለት የነበረ ሲሆን፤ በኮቪድ 19 ምክንያት ውድድሩ እንዲራዘም መደረጉ ይታወሳል።

የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ውድድር ሲራዘምም በዓለም ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑም ታውቋል።

በቶክዮ ኦሎምፒክ ላይ 200 ከሚጠጉ ሀገራት የተውጣጡ ከ11 ሺህ በላይ አትሌቶች እንደሚካፈሉበትም ይጠበቃል።

በኮቪድ 19 ምክንያት የተራዘመው የ2020 የቶክዮ ኦሎምፒክ ከፊታችን ሐምሌ 16 ጀምሮ እንደሚካሄድ የሚጠበቅ ሲሆን፥ የፓራ ኦሊምፒክ ደግሞ ከነሃሴ 18 ጀምሮ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe