የአለም የሴቶች ማራቶን ሪከርድ ዛሬ በርሊን ላይ በኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ ተሰበረ!!

አትሌት  ትዕግስት የበርሊኑን ቢ ኤም ደብሊው የሴቶች ማራቶን በ2:11:53 በመግባት በኬኒያዊቷ ብሪጂድ ኮስጄ ከአራት አመት በፊት ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ2 ደቂቃና 14 ሰከንድ አሻሽላ በሰፊ ልዩነት የሰበረችው። ከትዕግስት ተከትላ 2ኛ የወጣችው ኬኒያዊቷ ቼፕኪሩ 6 ደቂቃ አካባቢ ዘግይታ ነው የገባችው። ታንዛኒያዊቷ ማግዳሊና በ2:18:41 ሶስተኛ ስትወጣ፣ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ዘይነባ ይመር በ2:19:07 አራተኛ በመሆን አጠናቃለች።
እዚያው በርሊን በወንዶች ምድብ በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያዊው ታደሰ ታከለ ውድድሩን በሶስተኝነት አጠናቋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe