የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ  ቅሬታቸውን በይፋ ለክልላቸው ሕዝብ ገለፁ

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ  ከተሾሙ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ  ቅሬታቸውን በይፋ ለክልላቸው ሕዝብ ገለፁ።

ርዕሰ መሰደተዳድሩ ይኸንን የገለጹት ለጀግኖች አቀባበል በሚል የሚተኮሰው ጥይት ማኅበረሰቡን  እየረበሸ በመሆኑ  ነው ያሉት። ገና ጦርነቱ ባላለቀበት ሁኔታ ጥይት አላግባብ እየባከነ መሆኑን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ድርጊቱ ኀላፊነት የጎደለው መሆኑን ነው የተናገሩት።

“ሁሉም ለቀጣይ ትግል መዘጋጀት ባለበት ወቅት ጥይትን ያለ አግባብ ማባከን ኀላፊነት የጎደለው ተግባር ነው” ብለዋ ርእሰ መሥተዳድሩ ዶ/ር ይልቃል፤

በመግለጫቸውም ከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጋር በተካሄደው ፍልሚያ በጀግንነት ተጋድሎ ያደረጉ የጸጥታ አካላት ለከፈሉት መስዋእትነት ትልቅ ክብር አለን ብለዋል። በግንባር ለተፋለሙ ጀግኖች አቀባበል ማድረግ ተገቢ ቢሆንም ለአቀባበል በሚል የጥይት ተኩስ ማድረግ ማኅበረሰቡን ረብሿል ነው ያሉት። ጦርነቱ ገና አለማለቁን እና ትግሉ ቀጣይ መሆኑን ያነሱት ርእሰ መሥተዳድሩ በዚህ መልኩ አቀባበል በመደረጉ የክልሉ መንግሥት ደስተኛ አይደለም ብለዋል።

በግላቸውም ይሁን በመንግሥት የታጠቁትን መሣሪያ በቁጠባ በአግባቡ እንዲጠቀሙም ጥሪ አቅርበዋል።

ጦርነቱ ሳይጠናቀቅ ጥይትን ማባከን የሀገሪቱንም ይሁን የክልሉን ኢኮኖሚ ስለሚያዳክም በየትኛውም አካባቢ የሚመለስ ኃይል ጥይት መተኮስ እንዲያቆም አሳስበዋል።

መስዋእትነት ለከፈሉ የጸጥታ ኀይሎች ከፍተኛ አድናቆት አለን ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ የመጨረሻው ድል እስኪገኝ ጦርነቱ እንደሚቀጥልም አስገንዝበዋል።

ከድል ማግስትም የጸጥታ ኀይሉ በሠራው ተጋድሎ ልክ እውቅና እንሰጣለን፤ ለመጪው ትውልድም እንዲታወስ እናደርጋለን ነው ያሉት።

SourceAMC

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe