የአማራ ክልል የፌደራል መንግስቱ ካሳ አድንዲከፍለው ሊጠይቅ ነው ፤

የአማራ ክልል መንግሥት ከሕወሃት ጋር ለተደረገው ጦርነት ላወጣው ግዙፍ ወጭ ፌደራል መንግሥቱ ካሳ እንዲከፍለው በይፋ ሊጠይቅ እንደሆነ የክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ ሃላፊ ግዛቸው ሙሉነህ ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል።

የክልሉ መንግሥት ምን ያህል ካሳ እንደሚጠይቅ ግን ገና ውሳኔ ላይ እንዳልደረሰ እና የተወሰነውን ወጭ ክልሉ ጭምር እንደሚጋራ ሃላፊው ገልጸዋል። የክልሉ መንግሥት ቀደም ሲል በጤናው መስክ ላወጣው ወጭ ብቻ ከፌደራል መንግሥቱ 2 ቢሊዮን ብር ጠይቆ የነበረ ሲሆን፣ በቅርቡ በአዲስ መልክ የሚያቀርበው የካሳ ጥያቄ ግን ሁሉንም መስኮች እንደሚያካትት ተገልጧል።

ክልልሉ 11 አባላት ያሉት አጥኚ ቡድን አዋቅሮ በክልል በህወሃት ታጣቂ ቡንድ የደረሰውን ውድምት ሲያጠና መክረሙን ሲሆን የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ይፋ ባደረገው ውጤት መሠረት በክል ከ279 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆን ንብረት መውደሙን አስተ፣መስታወቂ አይዘነጋም፤ ይህም ክልሉን ቢያንስ ወደ 30 ዓመት ወደ ኋላ እንደመለሰው ነው የተመለከተው፡፡

የፌደራል መንግስቱ በአማራ ክልል በጦርነቱ ሳቢያ  የሕወሃት ታጣቂዎች ምን ያህል ውድመት እንዳደረሱ የሚያጠኑ ቡድኖች አቋቁሞ እንቅስቃሴ እንደጀመረ አመልክቷል።

SourceReporter

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe