የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድን የፖርላማ ንግግር ተቃወመ፤

ጠቅላይ ሚኒስትሩ  “ዳኞች አንደኛ ደረጃ ሌቦች ናቸው” ማለታቸውን ያልተገባ ብሎታል፤

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሰሞኑን  በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ላይ፣ “ዳኞች አንደኛ ደረጃ ሌቦች ናቸው” በማለት ለተናገሩት ያልተገባ ንግግር ማስተካከያ እንዲያደርጉ የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር  ዛሬ ባሰራጨው ደብዳቤ መጠየቁን ተሰማ።

ልዩ ጥናትና ማስረጃ በሚፈልግ ጉዳይ ላይ ዐቢይ ዳኞችን በጅምላ በሌብነት መፈረጃቸው ተገቢ አይደለም ያለው ማኅበሩ፣ ንግግራቸው ሕዝብ በፍርድ ቤቶች ላይ ያለውን አመኔታ የሚያሳጣ፣ የፍርድ ቤቶችን ገጽታ የሚያበላሽ እና የምስጉን ዳኞችን ሞራል የሚጎዳ እንደሆነ ገልጧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የሙስና መንሰፋትን ለምክር ቤቱ  በስፋት ከገለፁ በኋላ በኢትዮጵያ አንደኛ ደረጃ ሌቦች ዳኞች መሆናቸውን ገልፀው ፖሊስ ፤ አቃቤ ህግና የዋና ኢዲተር መስሪያ ቤት ባለሙያዎች ከሁለት እስከ አራት ያለውን የሌብነት ደረጃ የያዙ ናቸው ማለታቸው ይታወሳል፤

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙስና የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱን ምክንያት በማድረግ  ህግ አስፈፃሚው አካል በህገ መንግስቱ እውቅና ያገኘውን ህግ ተርጓሚውን የፍትሕ አካል ጠንክር ባለ ቃላት ሲወቅስ የመጀመሪያ መሆኑ ተዘግቧል፤

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር ላወጣው መግለጫ የሰጠው ምላሽ የለም፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe