የአማርኛ ፊደላት ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቀረቡ
ብሔራዊ ፊደልን የብሔር ብሔረሰቦች የትምህርት መገልገያ መሣሪያ እንዲሆን የኢትዮጲያ ማህበራዊ ትስስር አነቃቂ ድርጅት የኢትዮጲያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን ጠየቀ፡፡
የኢትዮጲያ ማህበራዊ ትስስር አነቃቂ ድርጅት(Ethiopian social partnership Advocacy) በኢትዮጲያ የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በሴቶች በወጣቶች እንዲሁም በተለያዩ የማህበረሰቡ ክፍሎች የሚያስፈልጋቸውን አነቃቂ ስልጠናዎች በማዘጋጀት ተደራሽ ያልሆኑ የማህበረሰቡ ክፍሎችን ተደራሽ ለማድረግ የሚሰራ ድርጅት ነው።

