አሜሪካ የመርከቦችን እንቅቃሴ እያወኩ ነው ባለቻቸው የኢራን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ አዲስ ወታደራዊ ጥቃት ፈጽማለች፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን አካሄዷን ማስተካከል አለባት በማለት ካሳሰቡ በኋላ የአሜሪካ ጦር በፈጸመው ጥቃት በሆርሙዝ ሰርጥ የመርከቦችን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ የኢራንን ወታደራዊ ኢላማዎችን መትቻለሁ ብሏል፡፡
ኢራን በበኩሏ ባህሬን እና ኩዌትን ጨምሮ በቀጠናው በሚገኙት የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት ማድረሷን አስታውቃለች፡፡
የቴህራን የድርድር ቡድን ቁልፍ ሰው የሆኑት መሐመድ ባጋር ጋሊባፍ ሀገራቸው ከተኩስ አቁም ስምምነቱ እስካልተጠቀመች ድረስ ለስምምነቱ ተገዢ ሆና የምትቀጥልበት ምንም አይነት ምክንያት የለም ብለዋል፡፡
ቴህራን በአሜሪካ የተፈጸመባትን ጥቃት ተከትሎ በባህሬን፡ጆርዳን እና ኩዌት በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ የአጸፋ ርምጃ ወስዳለች፡፡
ኢራን አሜሪካ መሠረተ ልማቶቼን ካጠቃች ቀጠናዊ መሠረተ ልማቶችን እንደምታወድም አስጠነቀቀች፡፡
የኢራን ጦር ቃል አቀባይ በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ የሚደረግ ማናቸውም ጣልቃ ገብነቶች የቴህራን ሊጣስ የማይችል ቀይ መስመር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አሜሪካ የኢራንን መሠረተ ልማቶ ኢላማ ካደረገች ቀጠናዊ መሠረተ ልማቶችን እንደምታወድም ቴህራን ዛሬ ማስጠንቀቂያ መስጠቷን የፋርስ ዜና ወኪል አስነብቧል፡፡
የጦሩ ቃል አቀባይ መሠረተ ልማቶቻችንን ካጠፉ፤በምላሹ በቀጠናው የሚገኘውን ማንኛውንም ቀሪ መሠረተ ልማት እናወድማለን ብለዋል፡፡ ይህ የኢራን ከበድ ያለ ማስጠንቀቂያ የመጣው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ወደ ድርድር ጠረጼዛው ካልመጣች የሃይል አቅርቦቷና ድልድዮቿን ወደ ማጥፋት እናመራለን ካሉ በኋላ ነው፡፡//

