የአምባሰሏ ንግስት ማሪቱ ለገሰ ከ23 ዓመት ቆይታ በኃላ በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰች

የአንባሰሏ ንግስት በመባል የምትታወቀው የክብር ዶ/ር ማሪቱ ለገሰ ከ23 ዓመት የአሜሪካ ቆይታ በኃላ ዛሬ ታሕሳስ 24/2015 ወደ ኢትዮጵያ ተመልሳለች።

ዝነኛዋ ድምፃዊት ማሪቱ ለገስ ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስም በቤተሰቦቿ፣በሙያ አጋሮቿ እንዲሁም በአድናቂዎቿ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላታል።

ከ6 :00 ሰዓት ጀምሮም በብሄራዊ ቴአትር ለኹሉም ሰው ክፍት በሆነ መድረክ የእንኳን ደህና መጣሽ የተለያዩ የኪነጥበብ ዝግጅቶች እንደሚደረግ ተገልጿል።

ከአሜሪካ ሽኝት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችሁ ማሪቱ ለገስ፤ በኢትዮጵያ ቆይታዋ አዲስ አልበሟን ለአድማጭ የምታቀርብ ሲሆን፤ አዲስ አበባን ጨምሮ ደሴ እና በተለያዩ ከተሞች የሙዚቃ ሥራዋን እንደምታቀርብም ተነግሯል።

በዚህም መሰረት፤ ማሪቱ ታሕሳስ 29/2015 የመጀመሪያ ኮንሰርቷን በደሴ ከተማ እንደምታቀርብም አዲስ ማለዳ ያገኘችው መረጃ አመላክቷል።

በተጨማሪም የወሎ ዩኒቨርስቲ ከ7 ዓመት በፊት ያበረከተላትን የክብር ዶክትሬት ለአርቲስቷ በአካል እንደሚያበረክትም ታውቋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe