የአርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ስርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፀመ

የአርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ)  ቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹና የጥበብ አፍቃሪያን በተገኙበት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፀመ፡፡
የአርቲስቱን የህይወት ታሪክ ያነበበው አርቲስት ተፈሪ አለሙ እንደተናገረው፤ አርቲስቱ በህይወት እያለ ከፍተኛ ተከፋይ ቢሆንም የእኔ የግል ህይወት ይቅር ብሎ ለምስኪኖች ሲለግስ ኖሯል።

መርሀግብሩን በማስተባበር ላይ የሚገኘው አርቲስት ታምሩ ብርሃኑ በበኩሉ አርቲስቱ ሥራ ተብሎ የታዘዘውን ገፀ ባህርይ ሁሉ ወክሎ ብቻ ሳይሆን ሆኖ በብቃት መተወን ይችላል ያለ ሲሆን፤ ሌሎች አርቲስቶችም አብሬ ካልሰራሁ ብለው የሚመኙለት የተዋጣለት ባለሙያ እንደነበረም ገልጿል።

tariku baba

በመርሀግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው እንደተናገሩት፤ ከዓመታት በፊት የአይን ብሌኑን ለመስጠት ቃል በመግባቱነ ናተፈጻሚም በመሆኑ፤ በፊልሞቹም ጭምር ለትውልድ የሚተርፍ ስራ በመስራቱ በህይወት ባሉ ሰዎች አይን እና ልብ ውስጥ ህያው ሆኖ ይኖራል።እንደ ዶክተር ሂሩት ንግግር፤ በህፃጻንነት እድሜ አስቦ አይኑን ለማያውቃቸው ስዎች መለገሱ የሰውነት ጥግነቱን ያሳያል ብለዋል።
ዶ/ር ሂሩት በፊልሞቹ ሰውነትን ከራስ በላይ ሰው መኖርን ሲሰብክና የሰው ልጅን ህፀፅ በማሳየት የዜግነት ግዴታውን የተወጣ ነውም ሲሉ ተናግረዋል።በተሰጠው ጊዜ ከማንም በላይ እውቀቱንም አቅሙንም መጠቀም ችሏል ያሉት ዶክተር ሂሩት፤ በእኛና በልጆቻችን ልብ ውስጥ ይኖራል ብለዋል።
የኢትዮጵያ አይን ባንክ ተወካይ ሲስተር ሊያ ተካበው አርቲስቱ አይኑን መለገሱን የተመለከተ የምስክር ወረቀት ለታላቅ ወንድሙ አሸናፊ ብርሃኑ መስጠታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

የአርቲስቱ ስርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት dec 3  ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሥነ ስርዓት ተፈፀመ፡፡(ኢፕድ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe