የአክሱም ወረዳ ፍርድ ቤት “ተማሪዎች ሒጃባቸውን ለብሰው ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሱ” በሚል ውሳኔ አሳለፈ

ፍርድ ቤቱ “ተማሪዎች ሒጃባቸውን ለብሰው ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሱ” በሚል ውሳኔ አሳለፈ
 የአክሱም ወረዳ ፍርድ ቤት ሂጃብ መልበስ የሚከለክለው መመሪያ ላይ ዕገዳ ጣለ፤ በሂጃብ ምክንያት ተማሪዎችን ያገዱ ትምህርት ቤቶች ፍርድ ቤት እንዲቀርቡም አዟል!
የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሒጃብ ለብሰው እንዳይማሩ አስተዳደራዊ እግድ ባደረጉ 5 ትምህርት ቤቶች ላይ ክስ መመስረቱ ይታወቃል።
ጉዳዩ በዛሬው ዕለት የአክሱም ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርቦ ውሳኔ ተስጥቶበታል። ፍርድ ቤቱ አስተዳደራዊ እግድ ባደረጉ ትምህርት ቤቶች ላይ እግድ ጥሏል።
ጉዳዩ በተማሪዎቹ ላይ የማይቀለበስ የሰብአዊ መብት ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ተማሪዎቹ ሒጃባቸውን ለብሰው ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ የሚል ውሳኔ አስተላልፏል።
በሂጃብ ምክንያት ተማሪዎችን ያገዱ ትምህርት ቤቶች ለጥር 16/2017 ፍርድቤት ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ ትእዛዝ ተሰጥቷል።
በተያያዘ ዜና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰጠው ማሳሰቢያ ፥ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ዛሬ ጥር 6/2017 ዓ.ል ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ተጠናቋል።
የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ለመሳተፍ የሚያስችላቸው ፎርም ሳይሞሉ የተሰጠው የምዝገበ ቀነ ገደብ ዛሬ መጠናቀቁን አስታውሶ የዘገበው ሃሩን ሚዲያ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ይህንንና መሰል ጉዳዮችን በንቃት ይከታተላል።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe