ከሁለት ዓመት በፊት የቪዛ ገደብ የተጣለው የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ህብረት ሀገራት ውስጥ የገቡ ዜጎቹን መልሶ የመቀበል ትብብሩንን እንዲያሻሽል ግፊት ለማድረግ ነበር፡፡
በክልከላው የዲፕሎማት እና አገልግሎት ፓስፖርት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ያለ ክፍያ #ቪዛ እንዲሰጣቸው አይደረግም፣ ኢትዮጵያዊያን ቪዛ ለማግኘት የሚጠብቁት ጊዜ ከ15 የሥራ ቀናት ወደ 45 የሥራ ቀናት ከፍ እንዲል ያደረገ ነበር፡፡
የህብረቱ ኮሚሽን አደረኩት ባለው አዲስ ግምገማ መሠረት የኢትዮጵያ መንግሥት በህገ ወጥ መንገድ ወደ ህብረቱ አባል ሀገራት የሚገቡ ዜጎችን ለመቀበል በለተለይ ደግሞ የአደጋ ጊዜ የጉዞ ሰነዶችን መስጠት በኩል በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻሎች መኖራቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
በዚህም በኢትዮጵያዊያን ላይ ጥሎት የነበረውን የቪዛ ገደብ ማንሳቱን አስረድቷል፡፡
ከአንድ ወር በፊት የአውሮፓ ህብረት በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት አቋርጦት የነበረውን የበጀት ድጋፍ ዳግም ማስጀመሩ ይታወሳል፡፡
በዚህም ህበረቱ ለኢትዮጵያ መንግስት የበጀት ድጋፍ 140 ሚሊዮን ዩሮ ለመስጠት መወሰኑን ተናግሯል፡፡
የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የበጀት ድጋፍ መስጠቱን ያቋረጠው ከ6 ዓመት በፊት እ.አ.አ 2020 እንደነበር ይታወሳል፡፡

