የስታዲየሙን ማጠቃለያ ግንባታ ለማከናወን 18.6 ቢሊን ብር ተመደበ፡፡
የብሔራዊ ስታዲየም ምዕራፍ ሁለት ሎት ሁለትና ሦስት የማጠቃለያ ግንባታ ለማከናወን ነው ከ18 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ ይደረጋል የተባለው፡፡ ስታዲየሙን ለመገንባትና ለማጠናቀቅ 5 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ተይዞለት የተጀመረው ግንባታው ክ8 አመታት በሃላ 13 ቢሊዮን ብር ጭማሪ አሳይተል፡፡
በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ግንባታውን አጠናቆ ለማስረከብም የቻይናው ኮሙኒኬሽንስ ኮንስትራክሽን ካምፓኒ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ የምዕራፍ ሁለት ሎት ሁለትና ሦስት ስምምነት የፊፋን ደረጃ የጠበቁ የጣራ፡የቴክኖሎጂና የማስዋብ ውሎችን አካቷል ተብሏል፡፡
1ሺ200 መጸዳጃ ቤት፡800 የእጅ መታጠቢ ይኖሩታልም ተብሏል፡፡
ስራው ሲጠናቀቅም ስቴዲየሙ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮችን ማስተናገድ የሚችል እንደሆነ ተነግሯል፡፡

