የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከ226 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ማስመዝገቡ ተሰማ

 ከሀያት እስከ ጦር ሀይሎች ያለው የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በቅርቡ  ሊቋረጥ ይችላል ተብሏል፤
ገቢና ወጪው አልመጣጠን ያለው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖር ከ2010 ወዲህ ባሉት ዓመታት ከ226 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ማስመዝገቡን አቶ ሙሉቀን አሰፋ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ምክትል ስራ አስኪያጅ ተናገሩ፤
አቶ ሙሉቀን እንደገለፁት ቀደም ሲል የቀላል ባቡሩ ፕሮጀክቱ ጥናት ሲሰራ የባቡሮቹ ጥገና ማዕከል  አብሮ ባለመገንባቱ ባቡሮች ብልሽት ሲያጋጥማቸው በሀገር ውስጥ ለመጠገን ባለመቻሉ በርካታ የባቡር ፉርጎዎች  ከስራ ውጪ ለመሆን ተገደዋል ብለዋል፤ከ43 ባቡሮች በስራ ላይ ያሉት 22 ብቻ መሆናቸውን  በመጠቆም፤
የባቡር መለዋወጫ ዕቃዎችን በቀላሉ ከውጭ ሀገር ለማስመጣት የውጭ ምንዛሪ እክል የፈጠረበት የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የባቡር ዕቃዎች ብልሽት ሲያጋጥም ዕቃዎችን በሳጥን እያሸጉ ወደ ቻይና ለጥገና ለመላክ መገደዱ ተገልጧል፤
የከፋ የጥገና ችግር ያለባቸውን ባቡሮችን ሙሉ ለሙሉ በሀገር ውስጥ ለመጠገን ባለመቻሉም አንዳንድ እቃዎችን ከተበላሹ ባቡሮች ላይ በማውጣት ቀለል ያለ ብልሽት ባጋጠማቸው ባቡሮች ላይ ለመግጠምና የትራንስፖርት አገልግሎቱ እንዳይስተጓጎል ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አቶ ሙሉቀን ተናግረዋል፤
ከተሳፋሪዎች የሚሰበስበው የ4 ብር ክፍያ አዋጭ አለመሆኑን የሚገልፁ ስራ አስኪያጁ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት በባቡሮችና በባቡር መስመሮች ላይ የማስታወቂያ ስራዎችን ጀምሯል፤
ከማስታወቂያ ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘት ቢቻልም ገቢና ወጪውን ማመጣጠን ባለመቻሉ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ድጎማ እንዲያደርግ ተጠይቆ ፍቃደኝነቱን ገልጦ እንደነበር የተናገሩት አቶ ሙሉቀን አስተዳደሩ በዓመት 1. 5 ቢሊዮን ብር ለመደጎም ቃል ቢገባም ድጎማውን እስከዛሬ ድረስ እንዳልሰጠ ተናግረዋል፤
ሁኔታው በዚሁ ከቀጠለ ከሀያት እስከ ጦር ሀይሎች ያለው የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ሊቋረጥ እንደሚችል ስራ አስኪያጁ አስታውቀ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe