የአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ወደ ቴአትር ማሳያነት የመመለሱ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኗል ተብሏል፤

የአንጋፋው ሀገር ፍቅር ቴአትር ዕድሳት ስራ ተጠናቀቀ፤

የአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ወደ ቴአትር ማሳያነት የመመለሱ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኗል ተብሏል፤

በ1927 ዓ/ም ሀገርን ከጠላት ወረራ ለመታደግ ይቻል ዘንድ ሀገር ፍቅር ማህበር ተብሎ የተመሰረተውና ኋላ ላይ በ1960 ዓ/ም ሀገር ፍቅር ቴአትር ተብሎ እንደተቋቋመ የሚነገርለት አንጋፋው ቴአትር ቤት ታሪካዊ ይዘቱንና የምህንድስና ጥበቡን ሳይለቅ ዘመኑን እና የቴአትር ቤቱን ስም በሚመጥን መልኩ ዕድሳቱ ተጠናቆ የመጀመሪያ ርክክብ መደረጉን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክረትሪ ጽ/ቤት አስታወቀ፤

ላለፉት 20 ዓመታት አንዳችም ዕድሳት ያልተደረገለት ቴአትር ቤቱ የዕድሳት ስራው ወጪ ው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተመሸፈኑ ተነግሯል፡፡

610 መቀመጫዎች የሚኖሩት ዋናው የቴአትር ማሳያ አዳራሽን ጨምሮ የስዕል ማሳያ ሳሎን ፣አነስተኛ የቴአትር አዳራሽ፣ዘመናዊ የሙዚቃ መከወኛ ክፍል፣ካፊቴሪያ፣አስተዳደር ህንፃ እና ሌሎችም አገልግሎቶች የተካተቱለት ቴአትር ቤቱ ለተደራሲው ከፍ ያለ ምቾትን ከማጎናፀፉም በተጨማሪ የጥበብ ሰዎቹንም ለተሻለ የፈጠራ ስራ የሚያነሳሳ ምቹ እና ፅዱ የኪነጥበብ ቤት ሆኖ የዕድሳት ስራው ተጠናቋል ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል በ2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ወጪ እድሳት እንደተደረገለት የተነገረው የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ዋና ህንጻ አካ የሆነው የአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ መሠረታዊ እድሳት ተደርጎለትና ባለፈው ሳምንት የተመረቀ ቢሆንም ቴአትር ቤቱ እንደቀድሞው ለትርኢት ማሳያ በሩ ክፍት የመሆኑ ጉዳይ አጣራጣሪ መሆኑን የቴአትር ቤቱ አርቲስቶች ተናግረዋል፤

በርካታ አንጋፋ የቴአትርና የሙዚቃ ባለሙያዎችን ያፈራው ቴአትር ቤቱ ከከንቲባ ጽ/ቤት ጋር ተያያይዞ አገልግሎቱን ሲሰጥ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ከፀጥታ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ቴአትር ቤቱ ተዘግቶ አርቲሰቶቹም ወደሌሎች ቴአትር ቤቶች መበተናቸው ይታወሳል፤

ምቹ የተመልካቾች ወንበርና ሰፊ መድረክ ተገንብቶለት የተመረቀው ቴአትር ቤቱ ዳግም ወደ ቀድሞው አገልግሎቱ እንዲመለስ የብዙዎች ጉጉት ሲሆን የአስተዳደሩ ባህል፤ ቱሪዝምና ኪነጥበብ ቢሮ ቴአትር ቤቱ ስራውን እንዲጀምር ጥረት እያደረገ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe