የአዲስ አበባ አስተዳደር ሹምሽር እንደሚያደርግ ተሰማ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዚህ ሳምንት ውስጥ የካቢኔ ሹምሽር እንደሚያደርግ የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ። በምክትል ከንቲባነት አስተዳደሩን እየመሩ የሚገኙት ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) በዚህ ሳምንት የሚያደርጉትን ሹምሽር ለከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አቅርበው እንደሚያፀድቁ፣ ከታማኝ ምንጮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ይነሳሉ ተብለው ከሚጠበቁት ውስጥ ምክትል ከንቲባና የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊውን ሰለሞን ኪዳኔ (ዶ/ር) ጨምሮ የመሬት አስተዳደር፣ እንዲሁም የከተማው ፕላንና ልማት ኮሚሽን ኃላፊዎችና ሌሎችም መሆናቸው ታውቋል።

በተጨማሪም የትምህርት ቢሮ ኃላፊው፣ የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊውና የፍትሕ ቢሮ ኃላፊውም እንደሚነሱ ምንጮች ገልጸዋል።

በመሬት አስተዳደር ላይ የሚደረገው ሹምሽር መጠነ ሰፊ እንደሚሆን የገለጹት ምንጮች፣ ከቢሮ ኃላፊው እስከ ወረዳ ድረስ የሚገኙ የመሬት አስተዳደር ኃላፊዎች በሙሉ እንደሚነሱ አስረድተዋል።

የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በከተማዋ በተለያዩ ጊዜያት የሚከናወኑ የመሬት ወረራዎች፣ እንዲሁም በመሬት አስተዳደር ውስጥ ያለውን ችግር ሥር ነቀል በሆነ መንገድ ለመፍታት ታስቦ እንደሆነ ምንጮች ገልጸዋል።

ከሰሞኑ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ሹምሽር የሚነሱትን ኃላፊዎች በመተካት የአፋር፣ የሶማሌና የሐረሪ ተወላጆች የካቢኔ አባል ሆነው ይሾማሉ ተብሏል።

በአዲሱ ካቢኔ የሚካተቱት አብዛኞቹ አዲስ አበባ የተወለዱና የኖሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ሹምሽሩ በቀናት ውስጥ እንደሚካሄድና ለዚህም ሲባል የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ስብሰባ እንደሚጠራ ምንጮች ገልጸዋል።

Source: – Ethiopian Reporter

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe