የአዲስ አበባ አስተዳደር የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እገዳን ማንሳቱ ተሰማ!

የአዲስ አበባ አስተዳደር በጋራ መኖሪያና በንግድ ቤቶች ላይ ጥሎት የነበረውን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ህትመት እገዳ ማንሳቱን አስታወቀ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመሬት እና መሬት ነክ አገልግሎት ላይ ጥሎት ከነበረው እገዳ መካከል፣ በኮንዶሚኒየም እና ንግድ ቤቶች ላይ የጣለውን የይዞታ ካርታ ህትመት እገዳን በማንሳት አገልግሎት እንዲጀመር አዘዘ።

የከተማ አስተዳድሩ ካቢኔ ካቢኔ ከነሐሴ 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ አግዶት የቆየውን የመሬትና ይዞታ ነክ አገልግሎቶች በቅርቡ እንደሚያስጀምር ከጥቂት ሳምንታት በፊት መገለጹ ይታወሳል፡፡

በዚህ መሰረት የከተማ አስተዳድሩ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ጀማል አልይ ፣ ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ለሁሉም ክፍለ ከተሞች በፃፉት ደብዳቤ የከንቲባ ፅህፈት ቤት የጋራ መኖሪያ እና ንግድ ቤት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ህትመት ላይ ጥሎት የነበረውን ዕግድ ማንሳቱን አስታውሰው ፣ ክፍላተ ከተሞቹ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ መመርያ መስጠታቸውን የተገኘው ሰነድ ያሳያል፡፡

ሐላፊው የግብይት ስርዓቱና ልማት መስተጓጎል እንደሌለበት በመጥቀስ ለ 11 ክፍለ ከተሞች የተጻፈው ድብዳቤ የጋራ መኖሪያ ቤትና ንግድ ቤቶች ይዞታ ማረጋገጫ ህትመት የእዳ ማጣራት አገልግሎት እገዳ መነሳቱን ገልጸዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe