የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር 70/ 30 የተባለ አዲስ የመኖሪያ ቤት ፕሮግራም ሊጀምር ነው

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር 70 30 የተባለ ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት ማድረግ የሚያስችል ስምምነት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ተፈራረመ

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር 70 በመቶውን መቆጠብ የሚችሉ በማህበር የተደራጁ ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ መሰተዳድር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ ያስሚን ወሃበረዲን በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በቅርቡ ከ300 ሺ በላይ ቤቶች ለነዋሪዎች ተደራሽ የሆኑ ሲሆን በቅርቡ በርካታ አቅም ያላቸው ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት ማድረግ የሚያስችል ስምምነት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር መፈራረሙ ተገልጿል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የቤት ፍላጎት ለማሟላት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ከ 18 ዓመት ባለይ በ አብሮነት ሲሰራ የቆየ ሲሆን በአሁን ወቅት አዲስ 70 30 የተባለ የመኖሪያ ቤት ታለመገንባት ስምምነት አድርጓል ።

ከሁለት ዓመት በፊት በማህበር የተደራጁ 12 ሺህ የሚሆኑ አቅም ያላቸው ቆጣቢዎች ተመዝግበው የነበረ መሆኑ ተገልጿል ። በዚህም አራት ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ የሚሆኑት ቆጣቢዎች በአግባቡ መቆጠባቸው ተነግሯል ።

ለነዎሪዎች የቤት ባለቤትነት እውን ለማድረግ ከተማ አስተዳደሩ ባለ ዘጠኝ እና አስራ ሶስት ወለል መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ተገልጿል ።

በመሆኑም ነዋሪዎች 70 በመቶ የሚሆነውን በመቆጠብ 30 በመቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በብድር አገልግሎት በማግኘት የቤት ባለቤት የሚያደርግ ስምምነትን በዛሬው እለት መፈራረሙን ወይዘሮ ያስሚን ወሃበረዲን ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe