የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ ከ200 በላይ የተሽከርካሪ ስፖኪዮ ያዘ

” ስፖኪዮ የተሰረቀባችሁ ማስረጃ በማቅረብ ንብረታችሁን መውሰድ ትችላላችሁ ”

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ፤ በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ ከ200 በላይ የተሽከርካሪ ስፖኪዮ ጉድጓድ ውስጥ ተደብቀው መገኘታቸውን አስታውቋቃ።

ስፖኪዮዎቹን እየተቀበሉ በማከማቸት የተጠረጠሩ 2 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛልም ብሏል።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ አሜሪካን ግቢ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።

ተጠርጣሪዎቹ በአካባቢው በላስቲክ ተወጥሮ በተሰራ መኖሪያ ቤት ውስጥ ጉድጓድ ቆፍረው በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰረቁ በርካታ የመኪና ስፖኪዮዎችን አከማችተው የተገኙ ናቸው።

ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማና ፖሊስ ባደረገው ክትትል 2 ግለሰቦችን ከነኤግዚቢቶቹ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ የገለፀው ፖሊስ በተከናወነው ምርመራ የማስፋት ስራ የተሰረቁ ተጨማሪ ስፖኪዮዎች በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ጎላ ሚካኤል ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ እንደተመለሱ እና በአጠቃላይ 202 ስፖኪዮዎች ከነመፍቻዎቹ እንደተያዙ አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በተለያዩ ጊዜያት ስፖኪዮ የተሰረቀባቸው ባለንብረቶች ማስረጃዎቻቸውን በማቅረብና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል እየቀረቡ ንብረታቸው ስለመኖሩ አረጋግጠው እንዲረከቡ መልዕክቱን አስተላልፏል።

(አዲስ አበባ ፖሊስ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe