የአዲስ አበባ የድህነት ምጣኔ ጨምሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ የድሀነት ምጣኔ እየጨመረ መሆኑ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ኮሚሽን ከፍሮንተሪ አማካሪ ድርጅት ጋር ባደረገው ጥናት ከክፍለ ከተማ ክፍለ ከተማ የድህነት ሁኔታ ቢለያይም የድህነት ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከባለድርሻ አካላት በተደረገው ውይይት በጥናት መረጋገጡ ተገልጿል።

እንደ ፍሮንቴሬ አማካሪ ድርጅት ጥናት መሰረት በአዲስ አበባ ድህነት እየጨመረ መምጣቱ ዋና ዋና ምክንያቶቹ ፦

– በሀገሪቱ የተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ፣
– የመንግስት የማስፈፀም አቅም ውስንነት መኖሩ፣
– በከተማው ከጊዜ ወደ ጊዜ በተለያዩ ምክንያቶች የሰው ፍልሰት እየጨመረ መምጣቱ፣
– የስራ ዕድል ያለማግኘት፣
– ዝቅተኛ የስራ ባህል መኖሩ፣
– በመንግስት መስሪያ ቤት ሌብነት እና ብልሹ አሰራር መንሰራራት፣
– ህዝቡ የሚያነሳቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮች ቶሎ ምላሽ ማግኘት አለመቻላቸው ፣
– በተለያዩ ምክንያቶች ለበሽታ የተጋለጡ ዜጎች ራሳቸውን ችሎ ያለማስተዳደር እና ድጋፍ የሚሹ መሆናቸው፣
– በተለያየ ማህበራዊ ችግር እና የከተማው የህዝብ ብዛት በፍጥነት እየጨመረ መምጣቱ ከኑሮ ውድነት ጋር ባለመመጣጠኑ የተነሳ በከተማው ውስጥ የድህነት ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ጥናት አጥኚዎቹ ገልፀዋል።

የጥናቱ ተሳታፊዎች የተሻለ ውይይት በማድረግ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ተቀናጅቶ በመስራትና በከተማ ደረጃ የታዩ ችግሮችን መቅረፍ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ኮሚሽን ነው።

SourceAMN

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe