የአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

 

በአዲስ አበባ የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 89 በመቶ ወደ ቀጣይ ክፍል ማለፋቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ገለፀ። የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ዛሬ ከሰዓት በሰጡት መግለጫ ዘንድሮ ከተፈተኑ 70 ሺህ 525 ተማሪዎች መካከል 62 ሺህ 639 ተማሪዎች ወደ 9ኛ ክፍል ተዛውረዋል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ2010 ጀምሮ እየሰራቸው የሚገኙ ስራዎች ለውጤቱ መሻሻል ጉልህ ድርሻ እንዳላቸውም አንስተዋል። እንደከተማ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ 20 ተማሪዎች 13ቱ ከአዳሪ ትምህርት ቤት ሲሆኑ 3ቱ ከልዩ ልዩ ትምህርት ቤቶች መሆናቸውንም ጠቁመዋል። ተፈተኝ ተማሪዎች በትምህርት ቢሮው የማህበራዊ ሚዲያ ውስጥ በሚገኘው ሊንክ ገብተው ውጤታቸውን መየት እንደሚችሉም በመግለጫው ተገልጿል። የዘንድሮ የ8ኛ ክፍል ከፍተኛው ውጤት 97.3 ሆኖ ተመዝግቧል።

ውጤቱን ለማየት ከዚህ በማስከተል ያስቀመጥንላችሁን ማስፈንጠሪያ መጠቀም ትችላላችሁ 👉 https://aa.ministry.et/#/result

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe