የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችን ከግለሰብ ቤት አገኘ

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከሁለት ወር በላይ በፈጀ ክትትልና ጥናት በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተደብቆ የነበረ የጦር መሳሪያ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ግንቦት 7 ቀን 2012 ዓ/ም ከኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ቤተል አካባቢ በአንድ መኖሪያ ቤት 10 ሽጉጥ፣ 110 የሽጉጥ ጥይት 26 ክላሽን-ኮቭ ጠብመንጃ፣ 25 መሰል ባዶ ካርታ፣ ጥይት ለመሙላት የተዘጋጀ ባሩድ የተገኝ መሆኑን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ከበደ አስፋው ገልፀዋል፡፡

Read also:ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ደረጃ የውሃ ሙሌት ለመጀመር  የግብፅን ይሁንታ እንደማትፈልግ ለፀጥታው ምክር…

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ክልል ሲንቀሳቀሱ በተገኙ ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር በማዋል በግለሰቦቹ ምሪት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ክልል በመኖሪያ ቤት ውስጥ የተደበቀው የጦር መሳሪያ መያዙንሃላፊው አብራርተዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ሳጥን ተራ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ መጋቢት 22 ቀን 2012 ዓ/ም አንድ መትረየስ እና 7 ክላሽን-ኮቭ ጠብመንጃ ከተገኘ ጀምሮ ፖሊስ በወንጀሉ ላይ ተከታታይነት ያለው ጥናትና ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ኮማንደር ከበደ አስፋው ገልፀዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹንና የወንጀሉን ዱካ ለማግኘት የክፍለ ከተማ ኢንተለጀንስ አባላት ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውን ሃላፊው ገልፀው ለስራው ውጤታማነት መረጃ በመስጠት ለተባበሩት የህብረተሰብ ክፍሎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Read also:300 አውቶብሶችን ማቆም የሚችለው የቃሊቲ የአውቶብስ ዴፖ ተመርቀ

ወንጀል ፈፅመው ከህግ ተጠያቂነት የሚያመልጥ እንደሌለ ያብራሩት ሃላፊው ቤት አከራዮች ለማን እና ለምን ተግባር እንደሚያከራዩ በጥብቅ ማወቅ እንዳለባቸው እና አጠራጣሪ ነገር ካለ ለፖሊስ ጥቆማ መስጠት እንደሚጠበቅባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Read also:በአረንጓዴ አሻራ ከተከተሉት ችግኞች 84 በመቶ የሚሆኑት መጽደቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ…

ግለሰቦቹ የጦር መሳሪያዎቹን ለምን ተግባር እንደሚያውሏቸው ለማረጋገጥ ሂደቱ በምርመራ ላይ መሆኑን ሃላፊው ጨምረው ገልፀዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe