የአዴኃን ታጋዮች ከብአዴን ጋር የተደረገውን ውህደት በመቃወም ስብሰባ አድርገው አዲስ ሊቀ መንበር መረጡ!

ከኤርትራ በረሃ የትጥቅ ትግል በኃላ ወደ ኢትዩጲያ የገባው የአዴኃን ሰራዊት በባህርዳር የአማራ ክልል ፍትህ ማሰልጠኛ ተቋም ውስጥ ከ80% በላይ ታጋይ አባላት በወሰኑት ውሳኔ መሰረት አመራሮቹን መቀየሩ ይታወቃል። ነገር ግን የቀድሞወቹ አመራሮች ታጋዩችን ከበተኑ በኃላ ምንም ጉዳይ ባልታወቀበት ሁኔታ ከአዴፓ ጋር ተዋሃድን በማለት መግለጫ መስጠታቸው አይዘነጋም። ከአዴፓ ውስጥ ያሉት ያልተለወጡት አመራሮች በወሰዱት እርምጃ ለአዴኃን ታጋዩች እስከዛሬ ድረስ ቃል የተገባላቸው ጉዳይ ከመፈፀም ይልቅ ታጋዩች አንፈልጋቸውም በማለት ያባረራቸው የቀድሞ አመራሮችን ስልጣን በመስጠት ለፈፀሙት ወንጀል እንደመደበቂያ እየተባበረ ይገኛል። በመሆኑም ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ.ም በባህርዳር ቤንማስ ሆቴል አባላቱን ሰብስቦ ከለውጡ ሃይል በኤርትራ በረሃ ቃል የተገባላቸው 41 ነገሮች እስከዛሬ ድረስ አንዱም ባለመፈፀሙ ይህንን ቃል ለታጋዩቹ እንዲፈፀምላቸው በተጠናከረ መልኩ ለማስፈፀም ዳግም የይሁንታ ቀላቸውን የሰጡበት መድረክ በማመቻቸት ከለውጡ ሃይል ጎን ተሰልፈን እንዴት ጥቅማችንን አስከብረን ህዝብ ከተጋረጠበት ጥፉት መታደግ እንችላለን በማለት ውይይት ተካሂዷል። ከውይይቱ ባሻገር ለቀጣይ ድርጂቱን የሚመሩ ታጋዩችን ተመርጠዋል። በዚህም መሰረት ፦ 1ኛ. ታጋይ ተስፈሁን አለምነህ – የአዴኃን ሊቀመንበር 2ኛ. ታጋይ 50 አለቃ አበበ መልኬ – ም/ሊቀ መንበር 3ኛ. ታጋይ ጌታቸው ወዳጆ – የህዝብ ግንኙነት 4ኛ. ታጋይ ራስ ወርቅ መላኩ (ዳዊት) – የድርጂት ጉዳይ 5ኛ.ታጋይ ስለሽ ከበደ- የውጭ ጉዳይ 6ኛ. ታጋይ የሽዋስ እንዲሁም ሌሎች የስራ አስፈፃሚ አባላትን በመጨመር በአብላጫ ድምፅ ተመርጠዋል። በስብሰባው ብ/ጀነራል ተፈራ ማሞ ጨምሮ ኮነኔል ፈንታ ሙሃባው ፤ ከአብክመ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ም/ሀላፊ አቶ ገደቤ ሀይሉ እንዲሁም ከመኢአድ ዶ/ር ስዩም እና መቶ አለቃ ጌታቸው ፣ከወልቃይት የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አቶ መብራቱ ፣ ከአብን እና ከአርበኞች ግንቦት 7 ተወካዩች ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። በመጨረሻም ከታጋዩች የተሰጠን አስተያየት ጨምሮ ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ስብሰባው የቀጣይ አመራሮችን በመምረጥ ተጠናቋል።
Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe