የአገራዊ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና 62 ጥያቄዎችን የመለሱ / 80 ፐርሰንታይል ያገኙ ተማሪዎች በሚፈልጉበት ተቋም ገብተው መማር ይችላሉ ተባለ

የአገራዊ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ
” 62 ጥያቄዎችን የመለሱ / 80 ፐርሰንታይል ያገኙ ተማሪዎች በሚፈልጉበት ተቋም ገብተው መማር ይችላሉ ” ተብሏል
#Ethiopia | የትምህርት ሚኒስቴር ለኹሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና ለኹሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ የአገራዊ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (National GAT) የመቁረጫ ነጥብ አሳውቋል።
በዚህም መሠረት ፤ አጠቃላይ ከተፈተኑት ጥያቄዎች ውስጥ 62 (50 በመቶ) እና በላይ ጥያቄዎችን የመለሱ ወይም 80 ፐርሰንታይል (80 Percentile) ያገኙ ተፈታኞች ብቻ፤ ለመማር በሚፈልጉበት ተቋም አመልክተው መማር የሚችሉ እንደሆነ ተገልጿል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመልካቾች ለማመልከት ሲመጡ ውጤታቸውን እንዲያቀርቡ በማድረግ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ https://portal.aau.edu.et/…/ApplyForAdmis…/TestingStatus በመግባት እና የተማሪውን የመግቢያ ስም (Username) እና የይለፍ ቃል (Password) በመጠቀም ማረጋገጥ ይቻላሉ ተብሏል።
በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ መሰረት ፤ በኹሉም የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለመማር የሚፈልጉ አመልካቾች፤ በሙሉ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና (National Graduate Admission Test-NGAT) ተፈትነው ያለፉ ብቻ መሆን እንዳለባቸው አቅጣጫ መቀመጡ ይወሳል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe