የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ በቪዲዮ ኮንፈረንስ መካሄድ ጀምሯል

34ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ በቪዲዮ ኮንፈረንስ መካሄድ ጀምሯል።

በዓለምአቀፉ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በቪዲዮ መካሄድ የጀመረው ስብሰባ እስከ ነገ እንደሚቀጥል ታውቋል።

መሪዎቹ በተመረጡ አጀንዳዎች ብቻ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ለዚህም በአህጉሩ ያለው ዝቅተኛ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት በምክንያትነት ተጠቅሷል።

በስብሰባው የሕብረቱ ኮሚሽነር ሙሳ ፋቂ መሃማት፣ የወቅቱ የሕብረቱ ሊቀመንበር የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪ ራማፎሳ እንዲሁም የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሌክስ ሺሴዴኬ ንግግር አድርገዋል።

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሌክስ ሺሴዴኬ ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪ ራማፎሳ የወቅቱን የሕብረቱ የሊቀመንበርነት ይረከባሉ።

በ34ኛው የመሪዎች ስብሰባ የሕብረቱ ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሃማት እና ምክትላቸው ኮይሲ ኳርቴንን ለመተካት ምርጫ እንደሚካሄድም ታውቋል።

በሌላ በኩል በአፍሪካ አምስት ቀጣናዎች የተከፋፈሉ የተለያዩ ኮሚሽነሮች ምርጫ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማርያምን ለሕብረቱ የትምህርት፣ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ኮሚሽነርነት ዕጩ አድርጋ አቅርባለች።

ዛሬ በተጀመረው የቪዲዮ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎችና ርዕሳነ-ብሔራት ታድመዋል።

Sourceኢዜአ
Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe