የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዎች በገንዘብ እና በቪላ ሽልማት ተንበሸበሹ

የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የሆነው ኮትዲቯር እና ሁለተኛ የወጣው የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች የገንዘብ እና የቤት ሽልማት እንደተበረከተላቸው ቢቢሲ ዘግቧል።
የዋንጫው ባለቤት የሆነቸው ኮትዲቯር ተጫዋቾች እያንዳንዳቸው 82 ሺህ ዶላር እና ተመሳሳይ ገንዘብ የሚያወጣ ቪላ ቤት እንደሚያገኙ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የአፍሪካ ዋንጫን ያስተናገደችው ኮትዲቯር ፕሬዝዳንት አላሳኑ ኦታራ “ለዜጎቻችን በሙሉ ደስታን አስገኝታችኋላ” በማለት ተጫዋቾቹን አወድሰዋል።
በወድድሩ በአይቮሪ ኮስት ተሸንፈው ሁለተኛ የወጡት ናይጄሪያውያንም ወደ አገራቸው ሲመለሱ የጀግና አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ሱፐር ኢግልስ 2-1 በሆነ ውጤት ተሸንፈው ዋንጫውን በማጣታቸው የናጄሪያውያን ልብ ቢሰበርም፣ ያደረጉት ጥረት በፕሬዝዳንት ቦላ ቱኒቡ ሽልማት እና እውቅናን አግኝቷል።
እያንዳንዱ የናይጄሪያ ቡድን አባል የአገሪቱን ከፍተኛውን የክብር ሽልማት የሚያገኝ ሲሆን፣ በተጨማሪም የመኖሪያ አፓርታማ እና ከዋና ከተማዋ አቡጃ አቅራቢያ መሬት እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።
ነገር ግን የናይጄሪያ ተጫዋቾች ምን ያህል የገንዘብ ሽልማት ከመንግሥት እንደሚበረከትላቸው አልታወቀም።
ለደረጃ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ጋር ገጥማ በማሸነፍ በውድድሩ ሦስተኛ የወጣችው የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችም እያንዳንዳቸው 52 ሺህ ዶላር እንደሚበረከትላቸው የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe