የኢራኑ የበላይ መሪ ሞጅታባ ካሚኒ አሜሪካ እና እስራኤል ለፍርድ ይቅረቡ ሲሉ ጠየቁ

ጠቅላይ መሪው ይህን ጥያቄ ያቀረቡት ለሀገሪቱ የፍትህ አካላት ሲሆን  ሁለቱም ሀገራት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች የጦር ወንጀል ክስ እንዲመሰርቱ ጠይቀዋል፡፡

ሞጅታባ ካሚኒ በቅርብ ጊዘያት ውስጥ እስራኤል እና አሜሪካ የፈጸሙትን ጥቃት የኢራን የፍትህ አካላት አጥብቀው እንዲከታተሉት አሳስበዋል፡፡

ሀገራቱ በኢራን ላይ ያደረሱት ዘርፈ ብዙ ጉዳት በሺዎች የሚቆጠሩ የክስ መዝገቦችን መክፈት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የትኛውም በሆርሙዝ ሰርጥ የሚደረግ እሰጣ ገባ ውጥረቱን ከማባባስ ውጭ ሌላ ትረጉም የለውም አለ፡፡

ከፍተኛ የኢራን ዲፕሎማቶች ትላንት እሁድ በሰጡት አስተያየት በሰርጡ ላይ የሚደረግ የትኛውም እንቅስቃሴ ውጥረቱን ያባብሳል ብለዋል፡፡

የኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በኢራቅ ዋና መዲና ባግዳድ ትላንት እሁድ ባደረጉት ንግግር ከባህረ ሰላጤው ሀገራት ጋር የደህንነት ማዕቀፍ እንዲገነባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሚኒስትሩ ኢራን እየተሰራበት ካለው አሰራር ውጪ አዲስ ወይም የተለየ ዝግጅት ለመተግበር የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ ሁኔታዎችን ይበልጥ ወደተወሳሰበ ደረጃ የሚያመራ እና የሆርሙዝ ባህረ ሰላጤን ዳግም ለመክፈት በሚደረገው ሂደት ላይ መዘግየትን ይፈጥራል፤ውጥረቱንም ይጨምራል በማለት ገልጸዋል፡፡

የጭነት መርከቦች በስትራተቴጂካዊ የውሃ መስመር ውስጥ በኢራን ያልተፈቀደውን መተላለፊያ መስመር መቀጠም ቀጥለዋል ሲል አረብ ኒውስ ጽፏል፡፡

የእስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በሰጠው መግለጫ ኦማን እና የአለም አቀፍ የባህር ላይ ድርጅት ቴህራንን ሳያማክሩ አዲሱን የባህር ላይ ኮርደር ይፋ ማድጋቸውን ገልጾ፤መርከቦች መስመሩን እንዳይጠቀሙ አስጠንቅቋል፡፡

የሚኒስትሩ ማስጠንቀቂያ የመጣው የዩናይትድ ስቴትስ ጦር በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ በኩል በሚጓዝ መርከብ ላይ ለተሰነዘረው ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ቅዳሜ እለት በኢራን ውስጥ ባሉ በርካታ ኢላማዎች ላይ አዲስ ጥቃት መፈጸሙን ካስታወቀ በኋላ ነው፡፡

ቴህራንም በበኩሏ በባህረ ሰላጤው በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት በማድረስ ምላሽ መስጠቷ ይታወቃል፡፡

ሰሞንኛው የሁለቱ ሀገራት የጥቃት ልውውጦች አራት ወራትን ያስቆጠረውን እጅግ አውዳሚ ጦርነት በድርድር ለማጠናቀቅ የተጀመረውን ጥረት እየፈተነው ይገኛል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe