የኢትዮጵያ መንግስት በ72 ሰዓት ከአገር እንዲወጡ ትዕዛዝ የተሰጣቸው 7 የተመድ ሰራተኞች ህወሃትን ይረዱ ነበር አለ

ሚኒስቴሩ በ72 ሰዓት ከአገር እንዲወጡ ትዕዛዝ የተሰጣቸውን 7 የተመድ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰራተኞችን አስመልክቶ ፈጽመዋል ያለውን ህገ ወጥ ተግባራት ይፋ አደረገ
 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያየዩ የተመድ ድርጅቶች ተቀጠረው የሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት እንዲሰጡ በሚሰሩበት ወቅት ከሙያቸው ሥነ ምግባር ውጭ የተንቀሳቀሱ ሰባት ግለሰቦች ተግባርን ይፋ አድርጓል።
በውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ከተልዕኳቸው ውጪ የሚንቀሳቀሱ 7 የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ተወካዮች በ72 ሰዓታት ውስጥ ከአገር እንዲወጡ መንግስት በትናንትናው ዕለት መግለጹ ይታወሳል፡፡
የእነዚህ ባለሙያዎች ከባድ ጥሰቶች ለሚመለከታቸው የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ለሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች በተለያዩ አጋጣሚዎች ቢቀርቡም ምንም ምላሽ አለማግኝቱን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፡፡
ይህን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በተለያየዩ የተመድ ድርጅቶች ተቀጠረው በሚሰሩበት ወቅት ከሙያቸው ሥነ ምግባር ውጭ ተንቀሳቅሰዋል የተባሉት የሰባት ግለሰቦችን እኩይ ተግባራት ይፋ አድርጓል፡፡
ሚኒስቴሩ በመግለጫው በመንግስት የተወሰደውን እርምጃ በተመለከተ ግራ መጋባትን ለማስወገድ የሚከተሉትን የተመድ ከፍተኛ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰራተኛች ጥሰቶች የሙያ ሥነ -ምግባር ደንባቸውን በመጣስ ሲንቀሳቀሱ ነበር ብሏል፡፡
የተመድ ባለሙያዎች ከፈጸሟቸው ህገ ወጥና ኢ -ሥነ ምግባራዊ ተግባራት መካከል፤
1. ለተቸገረውና ዕርዳታ ለሚያስፈልገው ህዝብ ተብሎ የመጣን የሰብዓዊ ድጋፍና ዕርዳታ ለህወሃት አሳልፎ መስጠታቸው
2. ከመንግስት ጋር የተደረገን ስምምነት መጣሳቸው
3. የተለያዩ መገናኛ መሳሪዎችን ህወሃት እንዲጠቀምበት ማስተላለፋቸው
4. ለሰብዓዊ ደጋፍ የሚውሉ ቁሳቁሶችን ይዘው ወደ ትግራይ የገቡና ሳይመለሱ የቀሩ ተሽከርካሪዎች በህወሃት ቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ለወታደራዊ ተግባር መዋላቸውን እያወቁ እንዲመለሱላቸው ለመጠየቅ ተደጋጋሚ ቸልተኝነት ማሳየታቸው እና
5. ሀሰተኛና የተዛቡ መረጃዎችን ማሰራጨታቸውና ሰብዓዊ ድጋፍን ለፖለቲካ ዓላማ እንዲውል ማድረጋቸው የሚጠቀሱ ናቸው ብሏል።
መንግስት በአገር ውስጥ ሲንቀሳቀሱም ሆነ ዕርዳታ ሲሰጡ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የማያደፈርሱ እና ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት ከማይፈጥሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ሆነ ከሌሎች አጋር ኤጀንሲዎች ጋር በትብብር እንደሚሰራ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe