የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ሚዲያዎች ትግራይ ገብተው እንዲዘግቡ ፈቀደ !

መንግሥት ቢቢሲ እና ሮይተርስን ጨምሮ 7 ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ትግራይ ክልል ገብተው ስላለው ሁኔታ መዘገብ እንዲችሉ ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ።

በተጨማሪ በመጀመሪያው ምዕራፍ በክልሉ ስላለው ሁኔታ መዘገብ እንዲችሉ የተፈቀደላቸው የሚድያ ተቋማት ኤ.ኤፍ.ፒ፣ አልጀዚራ፣ ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ፍራንስ 24 እና ፋይናንሺያል ታይምስ መሆናቸው ነው የተገለጸው።

መንግስት በትግራይ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ በተለያዩ አካላት የሚሰራጩ መሠረተ-ቢስ እና እና በፖለቲካ ሴራ የተሞሉ ሐሰተኛ መረጃዎች አሳስቦኛል ብሏል።

ለትግራይ ክልል ሕዝብ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ የሚቀርበው ጥሪ የመንግሥትን ሉዓላዊ ሥልጣን እና ኃላፊነትን ከማንኳሰስ ከሚደረጉ የፖለቲካ ፍላጎቶች እና ወገንተኝነት የፀዱ ሊሆኑ እንደሚገባም መንግሥት አሳስቧል።

በትግራይ ክልል እየተከናወነ ስላለው የሰብአዊ ድጋፍ ፣ ሰብአዊ ተደራሽነት ፣ የሚዲያ ተደራሽነት፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት ምርመራዎች እና በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳድር እያከናወነ ስላለው ሥራም በመግለጫው ተብራርቷል።

የሰብአዊ ድጋፍን በተመለከተ በአብዛኛው ከሚነዛው “የሐሰት ወሬ” በተቃራኒ መንግሥት ከሀገር ውስጥ ከውጭ ድርጅቶች ጋር በሠራው ሥራ እስካሁን በክልሉ ከሚገኙ 36 ወረዳዎች መካከል በ34 ወረዳዎች ውስጥ ለሚገኙ 3.1 ሚሊዮን ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን ገልጿል።

በክልሉ የሰብአዊ ዕርዳታ ለማድረግ ላመለከቱ እና ዓለም አቀፍ መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ 135 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንዲሁም ሠራተኞች በክልሉ ተንቀሳቅሰው የሰብአዊ ድጋፍ ሂደቱን እንዲያግዙ ፈቃድ መሰጠቱን የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ ገልጿል።

SourceENA
Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe