የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚወዛገቡ ሁለቱን ኦነግ አመራሮችን  በተመለከተ ውሳኔ አስተላለፈ፤

  ጉባኤ ከመደረጉ በፊት የጉባኤው አጠራር ደንብ እንዲዘጋጅ አሳስቧል፤

            ምርጫ ቦርድ በኦነግ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት አስመልክቶ የቀረቡለትን አቤቱታዎች በማየት ውሳኔ መስጠቱን አስታውሷል።   በውሳኔው ቅር የተሰኙት የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር እነ አራርሶ ቢቂላ ጉዳዮን ወደፍርድ ቤት በመውሰዳቸው ክርክር ሲደረግበት ቆይቶ የሰበር ሰሚ ችሎት የሁለቱንም ወገኖች የመሰማት መብት በመጠበቅ አስተዳደራዊ ውሳኔ እንዲሰጥበት ወደቦርዱ መመለሱ ተገልጿል።  በዚህም መሰረት ምርጫ ቦርድ የተለያዩ ምርመራዎችን በማድረግ የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ ተከትሎ ውሳኔ አሳልፏል።

               ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ መጥራት እንደሚገባው ቦርዱ የገለፀ ሲሆን ፓርቲው እስካሁን ካለበት የአመራር ችግር አንጻር፣ ጉባኤ ከመደረጉ በፊት የጉባኤው አጠራር ደንብ እና የምርጫ ህጉን የተከተለ መሆኑን ማረጋገጥ ማስፈለጉን አስታውቋል።

               በዚህም የጉባኤ አጠራር ዝርዝር ዕቅድ፣ የጉባኤውን አጠራር በተመለከተ በተገቢው የፓርቲው አካል የተሰጠ ውሳኔ እና የውሳኔው ቃለጉባኤዎች እስከ ሚያዚያ 16 ቀን 2014 ዓ.ም እንዲቀርብ ወስኗል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe