ግንቦት 07/2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ በቀድሞ ህግ ሰርተፍኬት የነበራቸው እና በቀድሞው ህግ ምዝገባ ጀምረው ለነበሩ 106 ፓርቲዎች በአዲሱ ህግ ላይ የተቀመጡ መስፈርቶችን እንዲያሟሉ በደብዳቤ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡
Read also:ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ደረጃ የውሃ ሙሌት ለመጀመር የግብፅን ይሁንታ እንደማትፈልግ ለፀጥታው ምክር…
ከቦርዱ ደብዳቤ ከደረሳቸው 106 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል 76 የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰነዶችን ያቀረቡ ሲሆን በሕጉ መሠረት ተሟልቶ የቀረበ ስለመሆኑ እየተመረመረ ይገኛል፡፡
ምርመራውም
• ፓርቲዎቹ በደብዳቤ የተገለጸላቸውን ነጥቦች ሁሉንም ማሟላታቸውን ማረጋገጥ ( የህገደንብ ለውጥ ጠቅላላ ጉባኤ ሰነዶች አቀራረብ፣ የመስራቶች ፊርማ … የመሳሰሉት)
• የፖለቲካ ፓርቲዎች በሕጉ መሠረት ማሟላት የሚገባቸውን የመሥራች አባላት ብዛት ትክክለኛነትን ለመፈተሽ ካቀረቡት የመሥራች አባላት ዝርዝር ናሙና የማውጣት
• ናሙናዎቹ በትክክል ግለሰቦቹ የተፈረሙ መሆናቸውን ወደተፈረሙበት ቦታ በመላክ ማረጋገጥ
• የህገ ደንብ ለውጦችና፣ የጠቅላላ ጉባኤ ሰነዶች በትክክል መያያዛቸውን ማረጋገጥን ያጠቃልላል፡፡
Read also:ኢትዮጵያ ለኮረና ቫይረስ ፈውስ የሚሆኑ 45 ባህላዊ መድሃኒቶች ላይ ሳይንሳዊ ምርምር…
ይህ እንደተጠናቀቀም ሰነዶቻቸው ካስገቡት 76 ፓርቲዎች መካከል ምን ያህሎቹ መስፈርት እንዳሟሉ በቦርዱ ይፋ የሚደረግ ይሆናል፡፡
ነገር ግን የሚጠበቅባቸውን ሰነድ ማስገባት ያልቻሉ እና ጊዜ እንዲራዘምላቸው የጠየቁ 15 የፓለቲካ ፓርቲዎች መኖራቸውንም ቦርዱ ገልጿል።
አስራ ሶስት (13ቱ) አጥጋቢ ምክንያት ባለማቅረባቸው እንዲሰረዙም ቦርዱ ወስኗል፡፡