የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዲስ ህንጻ ግንባታ 1.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ማድረሱ ተነገረ

ብሄራዊ ቴአትር 1.5 ሚሊየን ብር ኪሳራ አደረሰ
የተጓተተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዲስ ህንጻ ግንባታ ከ1.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ማድረሱ ተነገረ::
በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ በ2011 ዓ.ም ላይ ግንባታው የተጀመረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዲስ ፕሮፌሽናል ህንጻ ግንባታ በጊዜው ባለመጠናቀቁ በመንግስት ላይ ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ኪሳራ አስከትሏል።
የህንፃውን ግንባታ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት በሶስት ዓመት ውስጥ ሰርቶ ለማጠናቀቅ ውል ቢያዝም ተቋራጩ ኩባንያ በነበረው ደካማ አፈጻጸም በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ቢያንስ 22% መስራት የነበረበት ቢሆንም መስራት የቻለው 6% ብቻ በመሆኑ በግንባታው ከፍተኛ መጓተት መፈጠሩን ተሰምቷል::
በአሁኑ ወቅት የዚህን ፕሮጀክት ግንባታ ስራ በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ ኦቪድ ግሩፕ ከተባለ አገር በቀል ድርጅት ጋር በቀጥታ ውል ተገብቶ የግንባታ ስራው በመፋጠን ላይ እንደሚገኝም የፌዴራል መንግስት ህንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ፕሮፌሽናል ህንጻ ግንባታን በቀጣይ ሦስት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ አዲሱ ተቋራጭ ኩባንያ ኦቪድ ግሩብ በ2.9 ቢሊዮን ብር ገንብቶ ለማጠናቀቅ እየሰራ መሆኑን የጽ/ቤቱ ኃላፊ ኢንጂር ዘሃራ አብዱልሃዲ አመልክተዋል።
via – ebc

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe