የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን – ስልጣን ሊለቁ የፈለጉበት ምክንያት ምንድነው?

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጠን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ በፍቃዳቸው ኃላፊነታቸውን እንደሚለቁ ገልፀዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ከስልጣን ሊለቁ የፈለጉበት ምክንያት ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጀ ግን ሀሰት መሆኑን ኢብባ አሳውቋል።

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አንዱአለም ፥ በቅርቡ ዶክተር ጌታቸው ድንቁ የተቋሙን ሰራተኞች ሰብስበው ተቋሙን እንደማይመሩና ኃላፊነታቸውን በፍቃዳቸውን ለመልቀቀ መወሰናቸውን አሳውቀዋል ሲሉ ገልፀዋል።

ዶክተር ጌታቸው ኑሯቸውን በአሜሪካ አድርገው ለማስተማር እና ለመርምር ስራ ወደኢትዮጵያ መመለሳቸው የተገለፀ ሲሆን ምክትል ዳይሬክተሩ አቶ ወንድወሰን ፥ ዋና ዳይሬክተሩ ወደኃላፊነት ሲመጡ ለ2 ዓመት ብቻ ለመስራት እንደሆነ ተናግረዋል ብለዋል።

በማስተማር እና በምርምር ስራ ጊዜያቸውን ማሳለፍ የበለጠ እንደሚወዱ የተናገሩት ዶ/ር ጌታቸው ለሰራተኞችም ያሳወቁት ይህንኑ ነው ፤ ከዛ ውጭ የሚናፈሰው በሙሉ ሀሰተኛ መረጃ ነው ሲሉ አቶ ወንድወሰን አሳውቀዋል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን (ኢብቦ) ተጠሪቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲሆን ጉዳዩ በቦርድ ውሳኔ እስከሚፀድቅ መልቀቂያቸው ተቀባይነት እስኪያገኝ ድረስ ኃላፊነታቸውን ለቀቁ ተብሎ መናገር እንደማይቻል ተገልጿል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe