የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋናና ም/ዳይሬክተሮች ከመጋቢት 1 ጀምሮ ከስራ መሰናበታቸው ተሰማ

ላለፉት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንን በዋና ዳይሬክተርነትና በምክትል ዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ የቆዩት ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ እና ምክትላቸው አቶ ወንድወሰን አንዱዓለም ከመጋቢት 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ  ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በወጣ ደብዳቤ ከስራ መሰናበታቸውን ተሰማ፡፡

ዋና ዳይረክተሩ ቀደም ብለው  ከሥልጣናቸው በገዛ ፍቃዳቸው እንደለቀቁ የተገለፀ ሲሆን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ግን ተመሳሳይ ደብዳቤ ስለማስገባታቸው የታወቀ ነገር የለም፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በቅርቡ በፖርላማ በፀደቀው አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ መሠረት ስያሜውን ወደ ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንነት የቀየረ ሲሆን መስሪያ ቤቱን የሚመሩ አዳዲስ የቦርድ አባላት በህዝብ ጥቆማ በፖርላማ እንደሚሰየሙ ይጠበቃል፡፡

<እናት ፖርቲ ብልፅግናንና ኢዜማን የሚፎካከር ፖርቲ ሆነ>

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን በዋና እና በምክትል ዋና ዳይሬክተርነት የሚመሩት ግለሰቦችም  ከማንኛውም የፖለቲካ ፖርቲ አባልነት ነፃ መሆናቸውን በማረጋገጥ በጠቅላይ ሚኒስተሩ አቅራቢነት በፖርላማ እንደሚሾሙ አዲሱ አዋጅ ይደነግጋል፡፡

<ቡና ባንክ መምህራንንና የጤና ባለሙያዎችን ሊሸልም ነው>

ላለፉት ሁለት ዓመታት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን በቦርድ ሰብሳቢነት እየመሩ ያሉት የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚልም በኢዲሱ አዋጅ መሠረት ከቦርድ ሰብሳቢነታቸው እንደሚነሱ ምንጮች አመልክተዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አስተዳደር ወደ ስልጣን እንደመጣ ቀደም ሲል የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋናና ምክትል ዳይሬክተር የነበሩትን የቀድሞ የህወሃት አመራሮች አቶ ዘርአይ አስገዶምና ምክትላቸውን አቶ ልዑል ገብሩ በአንድ ጊዜ  በማንሳት በአቶ ሰለሞን ተስፋዬ ተክቷቸው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ከሁለት ዓመት ተኩል በኋላ ሁለቱንም የስራ ሃላፊዎች በአንድ ጊዜ ማንሳቱ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe