የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን የስንዴ ቀጥተኛ ግዥ ለማድረግ ጨረታ አወጣ

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ የስንዴ ቀጥተኛ ግዥ ለማድረግ ጨረታ አወጣ!

ኮርፖሬሽኑ በዋናነት ስንዴን የሚገዛው ለገበያ ማረጋጋት መሆኑ ይታወቃል፡፡ሆኖም ባለፉት ጊዜያት እሱን ወክሎ ግዥ የሚፈጽመው በገንዘብ ሚኒስቴር ስር የሚገኘው የመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት እንደነበር ይታወሳል፡፡ስንዴ ከስትራቴጂክ ሸቀጦች መካከል ነው የሚካተተው፤ ከስትራቴጂክ ሸቀጦች ግዥ ደግሞ የሚመራው በገንዘብ ሚኒስቴር ነው ያሉ አስተያየት ሰጪ አሁን ላይ በመንግስት አቅጣጫ ኮርፖሬሽኑ ግዥውን በቀጥታ እንዲፈፅም ይሁንታ ማገኘቱን ይጠቅሳሉ፡፡

በዚህም መሰረት የዛሬ 6 አመት ግድም የእህል ንግድ እና ሌሎች ተቋማትን በመቀላቀል የተመሰረተው የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ለገበያ ማረጋጊያ የሚሆን 400 ሺ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ለመግዛት ጨረታ አውጥቷል፡፡ ቀደም ሲል መሰል የስንዴ ግዥ ሙሉ ለሙሉ በመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ስር ከመጠቃለሉ በፊት የእህል ንግድ ግዥ ያደርግ ነበር፡፡ ሆኖም የመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ከ10 አመት ወዲህ ከተመሰረተ አንስቶ በማእከል ግዥውን ሲመራ ቆይቷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe